በፓርቲና በመንግስት የተቀመጡ ግቦችን ውጤታማ ለማድረግ አመራሩ በትክክል የሚቆጠር ተግባር ማስመዝገብ አለበት ፦ አቶ ፍቅሬ አማን

Spread the love

የክልሉ ድጋፍና ክትትል ቡድን በካፋ ዞን እየተከናወኑ ያለውን አጠቃላይ ወቅታዊ የፓርቲና የመንግሥት ስራዎች አፈጻጸም የግምገማ መድረክ ተካሂዷል ።

በፓርቲና በመንግስት የተቀመጡ ግቦችን ውጤታማ ለማድረግ አመራሩ በትክክል የሚቆጠር ተግባር በማስመዝገብ ወቅቱ የሚፈልገውን ብልጽግናን ማረጋገጥ አለበት ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ተናግረዋል ።

አክለውም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተቀመጡ ግቦች ማለትም የዜሮ ግቦች፣ የሁለት ድጅት ግቦች፣ የአንድ ግቦች እና የ100% ላይ የተቀመጡ ግቦችን አመራሩ ውጤታማ ለማድረግ እና የሚታይ ውጤት ለማስመዝገብ የ90 ቀን ዕቅድ አካል በማድረግ ግቡን ማሳካት አለበት ብለዋል።

የካፋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ታከለ ታምሩ በዞኑ እየተከናወኑ ያሉ አጠቃላይ የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸም ዝርዝር ሪፖርት አቅርበዋል።

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በዞኑ እየተሰራ ያለው እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን ገልጸው በጥንካሬ የተመዘገቡትን በማስቀጠልና የታዩ ጉድለቶችን በአጭር በማረም በትክክል የሚታይ ዉጤት ለማስመዝገብ ከወትሮ በተለየ ጠንካራ ክትትል ማድረግ አለበት ብለዋልማለታቸዉን የዘገበዉ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ኮሙኒኬሽን ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *