




በዓሉ የሚከበረው በአለምአቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ዙር፣በሀገርአቀፍ ለ21ኛ ዙር እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ ለ4ኛ ዙር ነው።
በመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ም/ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ለኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር ለመውጣት በየተቋሙ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ተግባር በመለየት ጠንክረው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
በተጨማሪ እያንዳንዱ ግለሰብ ተጠያቂነትን በማስፈን ከውይይት ባለፈ በተግባር ሙስናን መከላከል ይጠበቅበታል ሲሉ ማሳሰባቸዉን የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።
