




በምዕራብ ኦሞ ዞን የዞኑ ሥራ ክህሎት መምሪያ የ2018በጀት አመት የ5 ወር እቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ አቅጣጫ ላይ ምክክር እየተደረገ ይገኛል።
በመድረኩ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምሩ ቦኒ እንደተናገሩት ለወጣቶች ሥራ እድል ፈጠራ የተያዙ በጀቶች በአግባቡ እና በወቅቱ ማሰራጨት እንደሚገባ አስታውቋል።
ወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ በማድረግ ሁለተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚገባ ዋና አስተዳዳሪ አስገንዝበዋል።
ለወጣቶች በገጠር እና በከተማ የሥራ እድል ፈጠራ የግንዛቤ ሥራዎችን በመስራት ወጣቶች እንዲለወጡ ምቹ ሁኔታ መፈጠር አለብን ብልዋል።
የዞኑ የሥራ ክህሎት መምሪያ ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ዶማ እንደተናገሩት ወጣቶች በየአካባቢው ያሉት ፀጋዎች ለይተው በመጠቀም እራሳቸውን እና አካባቢ እንዲለወጡ ልዩ ትኩረት ይሻል ነው ያሉት።
ለወጣቶች ምቹ እና አስተማማኝ የሥራ ዕድል በመፈጠር ሁለተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ ይጠበቃል ብልዋል።
በ5 ወራት ዉስጥ በጊዜያዊ እና በቋሚነት ከ2ሺህ 826 ወጣቶች የሥራ ዕድል መፈጠሩን አውስተዋል።
በዚህም የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ የብድር ስርጭትን በ5ወራት ዉስጥ 2.3ሚሊዮን ብር ለማሰራጨት ታቅዶ 800 ሺህ ብር የተሰራጨው በመሆኑ እንደ ድክመት አንስተው በዚህ ስርጭቱ ለማሻሻል ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸው አክሎበታል።
በመድረኩ የመምሪያው ባለሙያ እና የኦሞ ባንክ ጀሙ ዲስትሪክት ባለሙያዎች ዝርዝር የሆነ አፈጻጸም ለመድረኩ ተሳታፊዎች አቅርቧል።
መድረኩ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምሩ ቦኒ የዞኑ የፖለቲካ እና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አቤል ኢሳያስ እና የሥራ ክህሎት መምሪያ ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ዶማ መድረኩ እየመሩ ይገኛል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
