በክልሉ ያለዉ የተፈጥሮ ሀብት የአካባቢው ማህረሰብ ህይወት እንዲቀይርና ኑሮውን ማሻሻል እንዲያስችል ብዙ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ደን አካባቢ ጥበቃ አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ገለጸ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን አካባቢ ጥበቃ አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ከመልካ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የአካባቢና ማህበራዊ ተጽዕኖ ግምገማ ረቂቅ ደንብና መመሪያዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በሚዛን አማን ከተማ የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል፡፡

መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት ክልሉ ደን አካባቢ ጥበቃ አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኢንጂነር አስራት ገ/ማሪያም፤ ክልላችን በሀገራችን ካሉ አካባቢዎች በተፈጥሮ ሀብት ፀጋው ግንባር ቀደም ተጠቃሽ መሆኑን ጠቅሰው ይህም የተፈጥሮ ሀብት የአካባቢው ማህረሰብ ህይወት መቀየርና ኑሮውን ማሻሻል እንዲያስችል ክልሉ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ተግባራት እያከናወነ ያለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የተፈጥሮ ሀብቱን በዘላቂነት መጠቀምና ሀብት መፍጠር የተፈጥሮ ሀብቱን ከመጠበቅ ጋር ባልተጋጨ መንገድ ሊሆን ስለሚገባ ይህንን ሚዛኑን አስጠብቆ ለማስካሄድ ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ዶ/ር ኢንጂነር አስራት ገልጸዋል፡፡

የአየር ንብረት ለውጡ የአካባቢውን የአየር ንብረት ሚዛኑን ሳይዛባ ለትውልድ መተላለፍ አስፈላጊ በመሆኑ ለዚህም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ድርሻ ልወጡ ይገባል ብለዋል፡፡

በክልሉ ባለፉት አመታት የአካባቢና ማህበራዊ ተጽዕኖ ለመፍታት የተከናወኑ በርካታ ተግባራት ቢኖሩም ያልተሻገርናቸው በርካታ ችግሮች አሉን ያሉት ኃላፊው የተፈጥሮ ሀብቱን ማስጠበቅና የአየር ንብረቱን መቋቋም ሚዛናቸውን ጠብቀው እንዲሄዱ ህጎችን በማዘጋጀትና በእውቀት ማምረት ለነገ የማይባል ተግበር ነው ያሉት፡፡

ለዚህም ቢሮው ከመልካ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የአካባቢና ማህበራዊ ተጽዕኖ ግምገማ ረቂቅ ደንብና መመሪያዎች በማዘጋጀት ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ መሆኑን የቀረበውን ረቂቅ ደንብና መመሪያዎች ላይ ወይይት በማድረግ ለቀጣይ ሂደት ዝግጁ የሚደረግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በምክር መድረኩ በሚቀርቡ መሠረታዊና ህዝባዊ በሆኑ አጀንዳዎች ላይ ጠለቅ ያለ ውይይት በማድረግ በቀጣይ መስተካከል የሚገባቸው ረቂቅ ደንብና መመሪያዎቹ ግብአት የሚሆኑ ሀሳብ እንዲሰጡም ጠይቀዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የአካባቢና ማህበራዊ ተጽዕኖ ግምገማ ረቂቅ ደንብና መመሪያዎች ከመልካ ኢትዮጵያ በመጡ በዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች እየቀረበ ይገኛል፡፡

በመድረኩ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ጨምሮ የክልልና የዞን ሴክተር ኃላፊዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *