‎የመደመር መንግስት የሀይማኖት ተቋማት ለሀገርና ለትውልድ ግንባታ የከፈሉትን ዋጋ በሚገባ በመረዳት እውቅና ይሰጣል፦ አቶ አልማው ዘውዴ

Spread the love

‎የመደመር መንግሥትና የሀይማኖት ተቋማት በሚል መሪ ቃል ክልል አቀፍ የሙስሊም አባቶች ውይይት በቦንጋ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

‎በውይይት መድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ የመደመር መንግስትና የሀይማኖት ተቋማት ሚና በሚል መሪ ቃል በየደረጃ ካሉ የሀይማኖት መሪዎች ጋር ሰፊ ውይይቶችና ምክክሮች እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል።

‎ሀገራችን ኢትዮጵያ የሀይማኖት፤ የባህል፤ የቋንቋ ብዝሃነት የታደለች ሀገር በመሆኗ ይህ የብዝሃነት ፀጋ ህዝቦችን በማስተሳሰር ጠንካራ ሀገር ለመገንባት መሰረት ልሆን ይገባል ብለዋል።

‎የመደመር መንግስት ለሀይማኖት መቻቻልና መከባበር ትልቅ እውቅና መስጠቱን ገልፀው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለሀገር መንግስት ግንባታ የከፈሉትን መስዋዕትነት እውቅና ይሰጣል ብለዋል።

‎ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ለተጀመረው ትግል የሀይማኖት ተቋማት አሁንም ሚናቸውን በአግባቡ ልወጡ እንደሚገቡ ያሳሰቡት አቶ አልማው ልዩነቶችና አለመግባባቶች በውይይትና በምክክር የመፍታት ልምድን በማጎልበት የጋራ ሀገራዊ ትልሞችን ማሳካት ያስፈልጋል ብለዋል።

‎የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ሀላፊና የሰላም እሴት ማጎልበት ዘርፍ ሀላፊነት አቶ ምትኩ ታምሩ በተለይ የእስልምና እምነት አባቶች የሰላም እሴትን ለመገንባት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ እንደሞዴል የሚወሰድ መሆኑን ገልፀዋል።

‎መደመር መንግስት የሀይማኖት ሰኩራሊዝምን የሚያከብር መሆኑን ገልፀው የእስልምና እምነት ተቋማት ለበርካታ ዘመናት ስጠየቅ የነበረውን የመዋቅርና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንድፈቱላቸው ተገቢውን ድጋፍ አድርገዋል ብለዋል።

‎በንጉሴ ወልደየስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *