




ከበደ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል “የመደመር መንግስት እና የሐይማኖት ተቋማት ” በሚል መሪ ቃል ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ለኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አባቶች የተዘጋጀ ክልላዊ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
መድረኩ በሐይማኖት አባቶች ጸሎትና ቡራኬ የተጀመረ ስሆን የመደመር መንግስት እይታ ለሀይማኖት ተቋማት እና የመደመር መንግስትና የሀይማኖት ተቋማት ሚና በሚል መሪ ሀሳቦች ላይ ምክክር በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ መድረኩ የሚጠናቀቅ ይሆናል።
በመድረኩ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትልና የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ዓለሙ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው ለክልላችንና ለሀገራችን ከሐይማኖት ተቋማት የሚጠበቅበት እና መንግሥት ለሐይማኖት ተቋማት ያለው እይታ እና የሚሰራቸውን ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት የሚደረግበት መሆኑን ተናግረዋል።
ከዚህም ባሻገር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ለኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለሀገር ግንባታ ያላቸው ሚና እጅግ ከፍተኛ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊና የእለቱን ክብር እንግዳ አቶ ተመስገን ከበደ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያዊ ሀገራችን ስትገነባ ቋሚ ከሆኑ የሐማኖት ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ለኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተጠቃሽ መሆናቸውንና ለነዚህም የእምነት ተቋማት መንግስት በይፋ እውቅና ስሰጥ መቆየቱን ገልፀዋል።
እነዚህ የሐይማኖት ተቋማት ትውልድ በመልካም ስነምግባር እንዲታነጽና ሰብአዊነት እንዲሰመው በማድረግ ረገድ የማይተካ ሚና እንዳላቸውም ተናግረዋል።
የህብረተሰብን ትስስር በመፍጠርና ለኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ከፍተኛ ድርሻ እየተወጡ መሆኑን ያነሱት አቶ ተመስገን መንስት የሚተገብራቸው የልማትና የሠላም ተግባራትን የመደገፍ መልካም ተግባራትን እንደወትሮው ሁሉ አጠናክሮ ማስቀጠልና እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል።
በመድረኩ ከሁሉም ዞኖች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ለኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ወክለው የመጡ የሐማኖት አባቶችና የሚመለከታቸው አካላት እየተሳተፉ የሚገኝ ሲሆን የዕለቱን የመወያያ ሰነድ በክልሉ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ በአቶ ሀብታሙ ዓለሙ እያቀረበ ይገኛል።
በተከተል ወ/ሚካኤል
