




በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ”የመደመር መንግስት እና የሃይማኖት ተቋማት” በሚል መሪ ሃሳብ ከኢትዮጵያ ወንጌላውያን የኃይማኖት መሪዎች ጋር የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የክልሉ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ አንድድነት አሸናፊ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው የለውጡ መንግስት ከሃይማኖት ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር የአካባቢውን ሠላም እና ልማት ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የሃይማኖት ተቋማት ህገመንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው በነፃነት በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን በመጥቀስ የለውጡ መንግስት የበለፀገ ሀገርን ለመገንባት የጀመረውን መንገድ ለማስቀጠል የሃይማኖት ተቋማት ሚና የጎላ መሆኑን በመገንዘብ የሚጠበቅባቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ ሃላፊ እና የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ ፋጂዮ ሳፒ ከዚህን በፊት በነበሩት ስርዓቶች የሃይማኖት ተቋማት ላይ ይደርስ የነበረውን ጫና በማስታወስ የብልፅግና መንግስታት በሃይማኖት ተቋማት እና በመንግስት መካከል ያለውን ግንኙነት ሚዛናዊ በሆነ መልኩ በማስቀጠል የሀገርን ልማትና ብልፅግና ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
በኃይማኖት ተቋማትና በመንግስት መካከል ያለውን መተማመንና ትብብር በማጠናከር ለሠላም እሴት ግንባታና ለልማት ስራዎች ያላቸውን ሚና ማጠናከር እንደሚገባም ገልጸዋል።
የሃይማኖት ተቋማት ለሀገረ መንግስት ግንባታ እና ለአካባቢው ፀጥታ መስፈን የማይተካ ሚና እንዳላቸው ያብራሩት አቶ ፋጂዮ ኃይማኖታዊ ተቋማት አንድነትንና ሰላምን የሚያጠናክሩ አስተምህሮዎችን በማራመድ ለሠላም እሴት ግንባታና ለልማት ስራዎች ያላቸውን ሚና ማጠናከር እንደሚገባ በመግለፅ 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ፍትሐዊ እና ታዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚያስችሉ መልዕክተኞችን በማስተላለፍ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡም አሳስበዋል።
በአሁኑ ሰዓት የመወያያ ሰነድ እየቀረበ ይገኛል።
በካሳሁን አሰፋ
