በፍትሀብሔር ጉዳዮች ላይ በፍርድ ቤቶች አቅርቦ የመርታት አቅምን 90.5% ማድረስ መቻሉን የክልሉ ፍትህ ቢሮ ገለፀ

Spread the love

የክልሉ ፍትህ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በፍትህ አሰጣጥ ሂደት ውስጥ የመንግስትና የህዝብ ፍትሀብሔራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ አኳያ የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገቡን የቢሮ ኃላፊ አቶ እሼቱ ጎደቶ አብራርተዋል።

በበጀት ዓመቱ ቢሮው ከሳሽና መልስ ሰጪ በመሆን በ 1 ሺህ 7 የፍትሀብሔር መዝገቦች ላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ ክርክር ማድረጉን ያወሱት ኃላፊው ከነዝያ መካከል በ824 መዝገቦች ላይ ውሳኔ መሰጠቱን ገልፀዋል።

ውሳኔ ከተሰጠባቸው መዝገቦች ውስጥ በ 731 መዝገቦች ላይ ለመንግስት የተወሰነ ሲሆን ከዚህም 1.5 ሚልዮን ብር በላይ የመንግስት ሀብት ማዳን ተችሏል ብለዋል ኃላፊው።

ከዚህ በተጨማሪ በ አይነት 28 ሺህ 391 ካሬ የከተማ መሬትና 287 ሄክታር የገጠር መሬት በማዳን የህዝብና የመንንግስት ጥቅም ማስከበር መቻሉን ነው አቶ እሼቱ የገለጹት።

በተቃራኒ በተደረጉ ክርክሮች በ93 መዝገቦች በመንግስት ላይ የተወሰኑ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ በ 48 መዝገቦች ላይ ይግባኝ እንደተጠየቀባቸው የገለፁት ኃላፊው ለቀጣይ በጀት ዓመት አፈጻጸም ጠቋሚ ቁጥር መሆኑንም አንስተዋል።

በክልሉ አጠቃላይ በፍትሀብሔራዊ ጉዳዮች ላይ በፍርድ ቤቶች አቅርቦና ተከራክሮ የመርታት አቅምን 85% ለማድረስ ታቅዶ 90.5% አፈጻጸም ላይ መድረስ መቻሉን ኃላፊው ገልፀዋል።

በአሻግሬ ገ/ወልድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *