የክልሉን ህዝብ የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመፍታት ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል። ርዕሰ መስተደድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

Spread the love

የክልሉን ህዝብ የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመፍታት ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተደድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ በቤንች ሸኮ ዞን የተገነቡ የአጉና እና የዳማ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ከሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን መርቀው ከፍተዋል።

በክልሉ የልማት ጥያቄዎች ለመፍታት በተሰጠው ልዩ ትኩረት በተለያዩ የክልሉ አከባቢዎች በርካታ የልማት ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ማስመረቅ መቻሉን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣይ ሌሎች የልማት ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ የመፍታት ጥረቱ የህዝብ ልማት አቅም በማቀናጀት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በእንደኬል-ዲዙ መንገድ ዳማ ወንዝ ላይ የተገባው ድልድይ የጊድ ቤንች እና ሰሜን ቤንች እርስበርስ ከማስተሳሰርም ባሻገር ከአከባቢው ለገበያ የሚወጡ የግብርና ምርቶች በቀላሉ ተደራሽ በማድረግ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን የሚያሳድግ እንደሆነም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የገለጹት።

የብልጽግና ፓርቲ የዜጎችን ፍትሐዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሰጠው ትኩረት በክልሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ የቆሙ ፕሮጀክትን ማስጨረስና አዳዲስ ፕሮጀክቶች ጀምሮ ማጠናቀቅ መቻሉን የገለጹት የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ በዚህም የህዝቡን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የተጀመረው ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የለውጡ መንግሥት ለዞኑ ህዝብ ልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እየሰጠ ያለው አውንታዊ ምላሽ የሚደነቅ መሆኑ የገለጹት የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍቴን ለፕሮጀክቶቹ መጠናቀቅ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል።

በዳማ ወንዝ ከዚህ በፊት ድልድይ ባለመኖሩ 28 የአከባቢው ነዋሪዎች በውሃው መወሰዳቸውን በቁጭት የገለጹት አስተዳዳሪ አሁን ለተሰራው ልማት አመስገነው በሌሎች የዞኑ አከባቢዎችም የህዝብ የልማት አቅም በማስተባበር የልማት ስራዎች እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

የአከባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው የድልድይ መገንባቱ በአከባቢው የረዥም ጊዜ የልማት ጥያቄ መሆኑን በማስታወስ የክልሉ መንግሥት በአጭር ለህዝቡ የልማት ጥያቄ ለሰጠው ምላሽ ምስጋና አቅርበዋል።

ነዋሪዎቹ ቀጣይ በአከባቢው በሌሎች የልማት ስራዎች ላይም ከመንግሥት ጉን ቆመው ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *