በክልሉ ከ35 ሺህ በላይ ህብረተሰብ ክፍሎች በREDD+ ፕሮጀክት ተጠቃሚ መሆን መቻላቸው ተገለጸ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት አከባቢ፣ደን ፣ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ የREDD+ ፕሮጀክት የ2016 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2017 መሪ ዕቅድ ዙሪያ በሚዛን አማን ከተማ መክረዋል።

በመድረኩ የክልሉ አከባቢ፣ደን፣ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኢንጂነር አስራት ገ/ማሪያም በክልሉ በ2016 በጀት ዓመት በሬድ ፕላስ(REDD+)ፕሮጀክት በርካታ ህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ ተናግረዋል።

በክልሉ በፕሮጀክቱ የሚሰሩ ተግባራት በማህበረሰቡ ኑሮ ላይ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጡ ሀብቶችን በአግባቡ በመጠቀምና ከመረጃ ልውውጥ ጋር ያሉት ክፍተቶች ማረም ይጠበቃል ብለዋል ዶክተር ኢንጂነር አስራት ገ/ማሪያም።

የክልሉ የREDD+ ፕሮግራም አስተባባሪ ዶክተር የሪቾ ብርሃኑ ፕሮጀክቱ በክልሉ አምስት ክላስተሮች በ29 ወረዳዎች በተፈጥሮ ደን ጥበቃና በህብረተሰቡ ኑሮ ማሻሻል ላይ ሰፊ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተለይም በህብረተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ስራዎች በእርባታ፣በማሞከት፣በንብ ማነብ፣በማገዶ ምድጃ ቆጣብ እንዲሁም በጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመዋል።

በዓመቱ በደን ክለላ አሳታፍ ደን አስተዳደር 18 ማህበራቶችን በማደራጀት 113 ሺህ 581 ሄክታር መሬቶች መከለል እንደተቻለም አንስተዋል ።

ህብረተሰቡ ደኑን እየጠበቀና እየተንከባከበ ደኑን በማይጎዳ መልኩ ከደኑ ተጠቃሚ እንዲሆን ይሰራል ያሉት የፕሮጀክቱ አስተባባሪው በበጀት ዓመቱ ከ35 ሺ በላይ ህብረተሰብ ክፍሎች በREDD+ ፕሮጀክት ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ገልጸዋል።

በክልሉ በ29 ወረዳዎች በሬድ ፕላስ ፕሮጀክት ከ10 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅደው እስካሁን ከ6 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸው የተገለጸ ሲሆን ይህን የደን ሽፋን ለማሳደግ ትልቅ ሚና ይጫወታል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *