በመደመር መንግስት ዕይታ የዘርፎች እመርታ ስልጠና ላይ በተገኘው ክህሎት አመራሩ በአግባቡ በመጠቀም እቅዶች ማሳካት እንደሚገባ ተገለፀ።

Spread the love

በክልሉ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ በአቶ ነጋ አበራ የተመራው የድጋፍ እና ክትትል ቡድን ከምዕራብ ኦሞ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ጋር በቀጣይ ሥራዎች እቅድ ላይ ውይይት ተደርጓል።

በመድረኩ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ነጋ አበራ እንደተናገሩት አመራሩ በመፈጠር፤ በመፍጠን እና በዝላይ ዉጤት በሚመጣ መንገድ እና አማራጮች ሁሉ በጊዜ የለኝም መንፈስ በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

አመራሮች በመደመር መንግስት ዕይታ የተገኘው ክህሎት እንደ ምቹ እድል እና አጋጣሚ በመጠቀም ሁለተናዊ ብልጽግና በሚያረጋግጥ መንገድ ተግተው መስራት እንዳለባቸው ተናግሯል።

ሞዴል የሆነ የብልጽግና ህብረት ናቤተሰብ ፤የፓርቲ ህንጻ ግንባታ፤ የተማሪዎች የመማር ማስተማር ሥራዎች ፤ከተረጂነት ለመላቀቅ፤ ህገወጥ ኮንትሮባንዶች ቁጥጥር ፤የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች ማስፋት ፤ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸው አክሎበታል።

በዞኑ ያሉት አልሚ ባለሀብቶች በአግባቡ በመጠቀም ያለው መሬት በአግባቡ እንዲያለሙ የድጋፍ እና ክትትል ሥራ በሁሉም ዘርፍ ማጠናከር ይጠበቃል ብልዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምሩ ቦኒ በበኩላቸው በፈጠራ እና በፍጥነት በዉጤት ሊታጀብ የሚችል እቅድ ታቅዶ ሥራ መጀመራቸውን ጠቅሶ የድጋፍ እና ክትትል ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።

የፕሮጀክት እና የፕሮግራም አቅሞች በአግባቡ በመለየት በማቀናጀት ለዜጎች ተጠቃሚነት በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *