በባህዊ ክዋኔዎች የደመቀው ማሽቃሮ ባሮ በጌጫ!

Spread the love

የሸካቾ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ (ማሽቃሮ ባሮ) በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች ደምቀው ጌጫ ከተማ ተከብሮ ውሏል።

የሸካቾ የባህል መሪዎች ዘመኑ የሠላም፣የእርቅና የፍቅር እንዲሆን በዓሉን በምርቃት ነበረ የከፈቱት።

የሸካቾች የባህል አዋቂዎች በብሔረሰቡ ዘንድ በንግሥና ስርዓት፣የተከበረ እንግዳ ወደ አከባቢው ስመጣ እንዲሁም በሌሎች ባህላዊ ኩኔት የሚቀርበውን የሙዚቃና ውዝዋዜ (ዩቦ) በጋራ በማዘመን የብሔረሰቡን ቱባ ባህል ለበዓሉ ታዳሚዎች አሳይተዋል።

ከአጎራባች አከባቢዎች በበዓሉ ላይ የተገኙ ተጋባዥ እንግዶች በተለያዩ ባህላዊ ጨዋታዎች፣ እንዲሁም የፈረስ ጉግስ ትርዒት በዓሉ አድምቀው ውለዋል።

ማሽቃሬ ባሮ በሸካቾ ብሔረሰብ ዘንድ በወርሃ መስከረም የደረሰ አዝመራ እህል ተቀምሶ ቀጣዩ ዓመት የሠላምና የፍቅር እንዲሆን አባቶች በጋራ ወደ ፈጣሪ የሚማጸኑበት በዓል ነው።

የማንነት መገለጫ የኾነው የማሽቃሬ ባሮ በዓል በየአመቱ በአደባባይ በድምቀት የሚከበረ ህዝባዊ በዓል ነው።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *