ብልጽግና ፓርቲ የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነዉ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ”ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ማኒፌስቶ እና ምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

የፓርቲዉ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መርሐ -ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የብልጽግና ፓርቲ የ7ኛው ሀገራዊ የምርጫ ምልክት ”የሰንዴ ነዶ” ሲሆን ምልክቱ የመደመር ፣ አንድነት እና ትብብር መገለጫዎችን የያዘ ነዉ።

በመርሃ ግብሩ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ጨምሮ የክልልና የዞን ከፍተኛ የመንግስትና ፓርቲ አመራሮች፣ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *