ብልጽግና ትናንትን እያከመ ነገን በመተለም ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር እንዲትሸጋገር በቁርጠኝነት እየሰራ ፓያለ ፓርቲ ነዉ፦ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ማኒፌስቶ እና ምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል።

በመረሐ-ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እንደተናገሩት፤ የብልጽግና ፓርቲ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የተጋረጡ ውስብስብ ችግሮችን እየጠገነ አስደናቂ ስኬቶችን ማስመዝገብ ችሏል።

የኢኮኖሚ ልዕልና ለማረጋገጥ እንዲሁም የተዛባ መዋቅራዊ ችግር ለማረም፣ በሀገር ኢኮኖሚ ሪፎርም ማሻሻያ ፣ የውጭ ምንዛሬ፣ የማኅበረሰቡን ኑሮ ለማረጋጋትና የፋይናንስ እጥረት ለመቅረፍ በሰራዉ ሥራ ውጤቶች ተመዝግቧል።

ፓርቲዉ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በማሸነፍ ሀገሪቱን ለመምራት ከተረከበ ጊዜ አንስቶ በተለይም የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከማጠናቀቅ ባሻገር ከውጪ ይገባ የነበረው ሰንዴ ምርት በሀገር ውስጥ በማምረት የሀገር ሉዓላዊነት ማረጋገጥ መቻሉን ነዉ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የተናገሩት።

ብልጽግና ትናንትን እያከመ ነገን በመተለም ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር እንዲትሸጋገር በቁርጠኝነት የሚሰራ ፓርቲ እንደሆነም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የተናገሩት።

ፓርቲዉ በ7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ መንታ ግቦችን አንግበው መነሳቱን ያነሱት ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፤ምርጫው ሠላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻና በፍትሃዊነት በማካሄድ በአሸናፊነት በማጠናቀቅ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ዋነኛ ግቡ እንደሆነም ነው ያብራሩት።

በመደመር አስተሳሰብ የሚንቀሳቀሰው የብልጽግና ፓርቲ በቀጣይ የሀገሪቱ ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ፣ ምርትና ምርታማነት እንዲረጋገጥ ግብርናን ወደ ዘመናዊ እርሻ ማሸጋገር፣ የሀገርቱን ሉዓላዊነት የሚያስከብር የባህር በር ጥያቄ እውን በማድረግ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር እንደሚሰራም ተናግረዋል።

ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ጊዜያት የኢትዮጵያ ስብራቶችን በመጠገን፣ በብልፅግና ፓርቲ ስብራቶቿ እየተጠገኑ፤ እምቅ ሀብቶቿ እየወጡ ፤ የጂኦ ፖለቲካዊ ቁመናዋም እየተቀየረ ነዉ ያሉት ክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ናቸዉ።

ፓርቲዉ ህብረ-ብሔራዊ አንድነት፣ ኋላ ቀርና ድህንነት ለማሸነፍ ግጭትና ጦርነትን በውይይትና በምክክር ለመፍታት፣ ጠንካራ ዴሞክራሲና የፖለቲካ ሥርዓት ለመፍጠር እየሰራ የሚገኘው ስራ በቀጣይነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

አቶ ፍቅሬ አማን ብልጽግና ትናንትን በማከም፣ነገን በመተለም ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር በትጋት የሚሰራ ፓርቲ እንደሆነ ነው የጠቀሱት።

የብልጽግና ፓርቲ የ7ኛው ሀገራዊ የምርጫ ምልክት የሆነው የሰንዴ ነዶ” በመምረጥ የሀገሪቱን ብልጽግና ጉዞ እንዲትፋጠንም ጥሪ አቅረበዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *