የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የማህበረሰቡን ኑሮ የሚቀይሩ እና ተጠቃሚነታቸውን በተጨባጭ የሚያረጋግጡ ዜጋ ተኮር ሥራዎች በመሆናቸው ተጠናክሮ ይቀጥላሉ፦ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

Spread the love

ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት በክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ”በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ 4! በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ክልላዊ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ ንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል።

በብልጽግና ፓርቲ መሪነት ባለፉት ዓመታት ጀምሮ እየተከናወኑ የሚገኙ የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የማህበረሰቡን ኑሮ የሚቀይሩ እና ተጠቃሚነታቸውን በተጨባጭ የሚያረጋግጡ ዜጋ ተኮር ሥራዎች በመሆናቸው ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) አስታወቁ።

በመድረኩ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሥራዎች የአሳቢነት እና የአካፋይነት እሴት የሚያላብስ በጎ ተግባር እንደሆነም ተናግረዋል።

ባለፉት ዓመታት በክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የአረጋውያን ቤት ማደስ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ የአከባቢው ንጽሕና መጠበቅ፣በሴቶችና ህጻናት ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች፣የአረንጓዴ አሻራ እና በሌሎች መሠል ትኩረት መስኮች የማህበረሰቡን ህይወት የሚቀይሩ ስራዎችን በውጤታማነት በማከናወን ውጤቶች ተመዝግቧል ብለዋል ።

የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የማህበረሰቡን ኑሮ የሚቀይሩ እና ተጠቃሚነታቸውን በተጨባጭ የሚያረጋግጡ ዜጋ ተኮር ሥራዎች በመሆናቸው ተጠናክሮ ይቀጥላሉ ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለተግባሩ ስኬት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም አሳስበዋል።

የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የቡድን ስሜትን በመለበስ በአንድነት እና በመረዳዳት የዜጎችን ህይወት እና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ በጎ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል ።

በ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በ14 የትኩረት መስኮች 1 ሚሊዮን 33ሺህ ህብረተሰብ ክፍል ለማሳተፍ ዕቅድ መያዙን ጠቁመዋል።

በተግባሩም 2.4 ሚሊዮን ህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ያመላከቱት የቢሮ ኃላፊዋ፦በዚህም 980 ሚሊዮን የሚገመት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎች እንደሚከናወኑ ነው የገለጹት።

ለዕቅዱ መሳካት በየደረጃው የሚገኙ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዳጫወቱ እና በተግባሩ ሁሉም ዜጋ በበጎነት እንዲሳተፍም ጥሪ አቅርበዋል ።

የ2018 ዓ.ም የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራ በአቅመ ደካማ ቤት ዕድሳት በቦንጋ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *