




የሸካ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም እና የቀሪ ወራት ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የምክክር መድረክ በማሻ ከተማ እያካሄደ ነው።
በውይይቱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ እንደገለጹት ትምህርት የልማት ሁሉ መሰረት የዕድገት ሁሉ ቁልፍ መሳሪያ በመሆኑ በዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የሁሉም አካላት ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል።
ትምህርት ለትውልድ ትምህርት ቤቶችን ደረጀ ለመሻሻልና በትምህርት ግበአት ለመደገፍ የተሰራው ስራ የሚበረታታ ቢሆንም ህብረተሰቡን በማስተባበር ይህንን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አንስተዋል፡፡
የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ሞደል ቅድመ አንደኛ ክፍሎችን ማጠናከር በበጀት አመቱ በልዩ ትኩረት ይሰራም ብለዋል አቶ አበበ።
የትምርህት ዋና ማጠንጠኛው የተማር ውጤት ማሻሻል በመሆኑ ባለፉት ጊዜያት በትምህርት ዘርፍ ከተመዘገበውን ውጤቶች በመቆጨት ከገጠመን ስብራት ለመውጣት ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት በኃላፊነት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል ።
እንደ ሀገር ሁለንተናዊ ልማት ለማረጋገጥና ተወዳዳሪ የሆነ ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት ትምህርት ዋነኛ መሳሪያ ነው ያሉት የሸካ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ዓለሙ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለተማሪ ውጤት መሻሻል ሀገራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል ።
የመማሪያ መፅሐፍት አቅርቦትን ለማሻሻል ዘርፈ ብዙ ተግባራት በሁሉም መዋቅሮች ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
