በፖሊዮ ዘመቻ በተደረገው ሁሉ አቀፍ ርብርብ ከዕቅድ በላይ ማሳካት መቻሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ

Spread the love

የቢሮ ሃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በዘመቻው ለተሳተፉ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጽያ ክልል ከየካቲት 14 _ 17/2017 ዓ.ም በተደረገው የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ 552 ሺህ 2መቶ 46 ህፃናትን ለመከተብ ግብ ተጥሎ ወደ ስራ ተግብቷል።

አስፈላጊ ክትባቶችና የዘመቻውን ቁሳቁስ በማቅረብ ለባለሙያዎችና ሌሎች አጋዥ አካላት ስልጠና በመስጠት በሚዲያዎች በተለያዩ ማህበራዊ ሃይማኖታዊ ተቋማት የቅስቀሳና የግንዛቤ ማስጨ ስራዎች በትኩረት ተስርተዋል።

በዚህም ከየካቲት 14_17/2017 ዓ.ም የተደረገው የፓሊዮ ዘመቻ ከዕቅድ በላይ ያሳካንበት ነበር ብለዋል የቢሮ ኃላፊው አቶ ኢብራሂም ።

በዚህም 556 ሺህ 8 መቶ 43 ህፃናት የፖሊዮ ክትባት ማግኘታቸውን ጠቅሰው ይህም የዕቅዱ 101 ከመቶ መሆኑን ነው ያስታወቁት ።

ከዘመቻው ጎን ለጎን በተደረገው ቤት ለቤት አሰሳ

መድረስ ባማይቻልበት ሩቅ አካባቢ የሚገኙ ምንም ዓይነት ክትባት ያለገኙ ከ 2ሺ 8መቶ በላይ ህፃናትን እና ቆልማማ እግር ያላቸው ከሁለት አመት በታች 38 ከሁለት አመት በላይ 40 ህፃናትን አቀናጅቶ በመስራት መለየት መቻሉ የዘመቻው ሌላኛው ስኬት መሆኑን ጠቅሰዋል።

በዘመቻው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለነበራቸው የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ተቋማት የሃይማኖት አባቶች የጤና ባለሙያዎችና እና የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች የሴቶች ልማት ህብረት እና አጋር ድርጅቶች ለወላጆችና ትምህርት ተቋማት እንዲሁም በየደረጃው ያሉ የአመራር ሌሎች ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

አያይዘውም አሁን እየተሰራ የሚገኘውን የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን እንዲሁም የአፈጣጠር ዝንፈት ያለባቸው ህፃናት ልየታ በተገቢው በማገዝ ህክምና እንዲያገኙ ባለድርሻ አካላት የተለመደ ትብብራችሁን እንድትወጡ ሲሉ ኃላፊው አቶ ኢብራሂም ጥሪ አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *