በክልሉ በሴቶች ህብረትና ቤተሰብ ደረጃ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ስራ አስፈፃሚ አባላቱ በካፋ ዞን በሺሽንዳና በቦንጋ ከተማ አስተዳደር በሴቶች አደረጃጀቶች እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አስመልክቶ የመስክ ምልከታ አድርጓል።

በምልክታው በሺሽንዳ ከተማ በማህበር ተደራጅተው በእንጀራ በመጋገር ላይ የተሰማሩ ሴቶች የስራ እንቀስቃሴ እና በቦንጋ ከተማ በዲንቻ ህብረት ስር የሼ ሹኖ ዲጮኔ ብልጽግና ቤተሰብ የተሰሩ የንብ ማናብና የጓሮ አትክልትና የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝቷል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ የስራ አስፈፃሚ አባላት ቡድኑ የመስክ ምልክታው አላማ ሴቶች በሴቶች ክንፍ አደረጃጀቶች ስር ሆነው ተጠቃሚነትና ተሳትፎአቸውን ለማሳደግ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ለመቃኘት መሆኑ ተገልጿል ።

በካፋ ዞን በሺሽንዳ ከተማ እና በቦንጋ ከተማ በዲንቻ ህብረት ስር የሼ ሹኖ ዲጮኔ እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ የልማት ስራዎች በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑንና በክልሉ በሴቶች ህብረትና ቤተሰብ ደረጃ እየተከናወኑ ያሉ ልማታዊ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡

በክልሉ ጠንካራ የሴቶች ክንፍ አደረጃጀት እንዲኖሩ የሚያስችሉ በርካታ ውጤቶች መኖሩን እና በሌማት ትሩፋት እንዲሁም በሌሎች ተግባራት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ክንፉ የሴቶችን ተጠቃሚነት እና ተሳታፊነት ለማሳደግ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን መሰረት በማድረግ ባለፉት ሁለት ቀናት ሲያካሂዱ በቆዩት ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን የሴቶችን ተጠቃሚነትና ተሳትፎ በማላቅ ሁለተናዊ ብልፅግና ማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝ በመስክ ምልከታው ማረጋገጥ መቻላቸውን አንስተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *