በብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ውሳኔዎች እና በሴቶች ሚና ላይ የሚመክር ሀገር አቀፍ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል።

Spread the love

በመድረኩ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች እና የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አባላት እንዲሁም ደጋፊዎች በተገኙበት በቦንጋ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተካሂዷል።

ብልፅግና ፓርቲ የሴቶችን ሁለተናዊ አቅም በመጠቀም ተጠቃሚነታቸውን እና ተሳትፎአቸውን ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እየሰራ እንዳለ የተገለፀ ሲሆን ሁለንተናዊ ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ሴቶች ግንባር ቀደም ሚናቸውን በመወጣትና የፓርቲውን ማህበራዊ መሰረት በማስፋት የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ አቅጣጫ ስኬታማነት በጋራ መስራት እንደሚገባ በውይይቱ ላይ በሰፊ ተገልጿል።

የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ስራ አስፈፃሚ አባል ወ/ሮ የሺ ወልዴ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት የሴቶች ክንፍ የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተቀመጡ ተግባራት በብቃት ለመወጣት እንደ ሀገር ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንዳለ እና በቀጣይም በሀገር ደረጃ በሴቶች የሚነሱንና እየተነሱ ያሉ ጉዳዮች በብልጽግና ፓርቲ በዕቅድ ተካቶ የሚሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

የክንፉ ሁሉም አባላትና ደጋፊ ሴቶች ለሠላም፣ ለጋራ ተጠቃሚነት፣ ለውሳኔ ሰጪነት እና የኑሮ ውድነትን በመቀነስ የኢኮኖሚ አቅምን ለማሳደግ በግንባር ቀደምነት ሊታገሉ እንደሚገባ አሳስበው ሴቶችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ብቁ ማድረግ እንደሚያስፈልግ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ም/ቤት አባል ወ/ሮ ሱመያ ዳሳለው በክልሉ ያለው የሠላምና ፀጥታ ሁኔታ ለሌሎች ክልሎች በተሞክሮ ሊቀርብ የሚችል በመሆኑ ይህንን ሠላም ለልማትና ለልማት ብቻ ለማዋል መትጋትና አጠናክሮ ማስቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

የወል ትርክቶችን በማጽናት በጋራ ሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት አስፈላጊ መሆኑን የጠቆሙት ወ/ሮ ሱመያ ሴቶች ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ እየተደረገ የሚገኘው እንቅስቃሴ መኖሩን ጠቅሰው ሴቶች ራስን ማብቃት ላይ ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባም ተናግረዋል ።

በክልሉ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ጸጋ ከኢኮኖሚ ጋር በማስተሳሰር ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን ያሉትን ጸጋዎች ጎልተው እንዲወጡ በሚዲያ በተገቢው ማስተዋወቁ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚጠበቅ የቤንሻንጉል ክልል ዋና ኦዲተርና የሴቶች ክንፍ ኢንስፔክሽን ኮሚሽን ሰብሳቢ ወ/ሮ እናትነትሽ ማሩ አስገንዝበዋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሴቶች ክንፍ ወ/ሮ ሰብለጸጋ አየለ በበኩላቸዉ ብልፅግና ፓርቲ በሁለተኛ መደበኛ ጉባዔው ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች ተፈፃሚ በማድረግ በውይይቱ ላይ የተነሱ ጉዳዮች በቀጣይ የዕቅዱ አካል በማድረግ እንደሚሰራም አስረድተዋል።

ለዚህም የክልሉ የፖለቲካ እና ሴቶች ክንፍ አመራሮች የተቀመጡ ውሳኔዎችንና አቅጣጫዎችን ለሴቷ የማስረጽና ግንዛቤ የመፍጠር ሚናቸውን በተገቢው ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበው ለዚህም ሁሉም በየደረጃው የሚገኙ ሴቶች ተሳታፊ ለማድረግ በቁርጠኝነት የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በክልሉ ተጀምረው ያላለቁ የመንገድ እና ሌሎች መሠረተ ልማቶች ተጠናቆ ለአገልግሎት እንድበቁ ማድረግ፣ የሴቶች ወደ አመራርነት ከማምጣት ውስንነቶች መኖራቸውን፣ የሴቷን ተጠቀሚነት ሊያረጋግጡ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ማስፋፋት እና ሴቶችን ግንዛቤ ማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ ስልጠናዎች መስጠት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሠረት እንዳለበት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የሴቶችን ኢኮኖሚ ተጠቀሚነት ለማረጋገጥ የሴቶችን ተደማጭነት እና ውሳኔ ሰጪነት ላይ እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሁሉም ሴቶች የድርሻቸውን ለማበርከት እንደሚታጉ የገለፁት የውይይቱ ተሳታፊዎች በብልፅግና ፓርቲን ጠንካራ ፓርቲ ለማድረግ እህትማማችናትን የበለጠ ማጠንከር እንደሚገባ ተናግረዋል።

ሚዲያ ለአንድ ሀገር እድገት ወሳኝ በመሆኑ የብልፅግና ፓርቲ እሳቤዎች ለመስረፅ እና ለመተግበር በቀጣይም በፓርቲው ማዕቀፍ ውስጥ በመሆን ሚዲያን በተገቢው ለመጠቀም በቁርጠኝነት እንደሚሰሩም የውይይቱ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

በብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በአግባቡ በመፈፀምና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር በትኩረት እንደሚሰሩም አንስተዋል፡፡

ከድህነት ለማላቀቅ የግብርና ስራዎችንን ከወትሮው በተሻለ መንገድ ለመከናወን ውሃንና ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶቻችንን በመጠቀም የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ሴቶች ሚናቸውን በተገቢው ሊወጡ እንደሚገባ የውይይቱ ተሳታፊዎች ጠይቀዋል ።

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *