






በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቦንጋ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ በሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ የተወሰኑ የውሳኔ አቅጣጫዎች ላይ የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ህዝባዊ የውይይት መድረክ መካሄድ ተጀምሯል።
በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን የፓርቲው ብልጽግና ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ከቃል እስከ ባህል በሚል መሪ ቃል መካሄዱን ጠቅሰው በዚህም ስኬቶችንና ድሎቻችን ወደ ላቀ ደረጀ ሊያሻጋግሩ የሚችሉ ውሳኔዎችና የጋራ አቅጣጫዎች ተቀምጧል ነው ያሉት፡፡
በክልላችን አቅጣጫዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ የሴቶችን ተሳትፎ ተጠቃሚነትና አበርክቶ ጎልቶ እንዲወጣ ሰፊ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሚያደርገው ሁሉ አቀፍ ርብረብ በሴቶች ክንፍ ግንባር ቀደም መሪነት የሴቶችን ተሳታፊ ና ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተገ ይገኛል እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡
ስለሆነም ብልጽግና ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ለክንፉ አባላት እና ደጋፊዎች በማሳወቅና የጋራ መግባባትን በመፍጠር የሚነሱ ሀሳቦች በመቀበልና ችግሮቹን በመፍታት የትልሞቻችን አፈፃፀም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ይህ መድረክ የማይተካ ሚና እንዳለውም አስገንዝበዋል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ስራ አስፈፃሚ አባልና የአዲስ አበባ ብልጽግና ሴቶች ክንፍ ኃላፊ ወ/ሮ የሺ ወልዴ ፓርቲያችን ብልጽግና ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በውጤትና በስኬት ታጅቦ በተጠናቀቀበት ማግስት የሚደረግና እንደሀገር ሊያሻግሩን የሚችሉ መላው ህዝብ ሊፈጽሟቸው የሚገባቸው በርካታ ውሳኔዎች መወሰኑን ተናግረዋል፡፡
የመድረኩ ዋና ዓላማ ሴቶች በሁተኛው ብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ የተወሰኑ ውሳኔዎችን በተገቢው በመፈፀም ሁላንታናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ እንዲያችል ለማድረግ ያለመ የውይይት መሆኑንና እስከ ታችኛው ብልጽግና ቤተሰብ ደረጀ የሚዘልቅ በመሆኑ ለዚህም ሴቶች የራሳቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰብለጸጋ አየለ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የክልሉ ብልጽግና የፓርቲው አንድ አካል በሆነው የሴቶች ክንፍ 150 ሺህ በላይ ሴቶችን አባል አባል በማድረግ በቤተሰብና ህብረት እያደራጀና እያጠናከረ በአደረጃጀቱ ሴቶች እንዲወያዩና በጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ ግንባር ቀደም ሆነው በብልጽግና ፓርቲ ወደ ፊት እንዲመጣ በማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል፡፡
ብልጽግና ፓርቲ በሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ የተወሰኑ የውሳኔ አቅጣጫዎች ሴቶችን ያማከሉና የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እንዲሆኑ የሴቶችን ክንፍ ትልቁ ድርሻ እንዳለውም በንግግራቸው አንስተዋል፡፡
በተከተል ወ/ሚካኤል
