የምገባ መርሃ-ግብሩ ተማሪዎች ትምህርታቸው ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አስችሏቸዋል -የቤንች ሸኮ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ አገኘሁ ወርቁ

Spread the love

‎በሚዛን -አማን ከተማ በአማን አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች የምግባ ፕሮግራም በይፋ ተጀምሯል።

‎የትምህርት ቤት የምገባ መረሐ -ግብር መተግበር ለትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት የችግሮቹ ቁልፍ የመፍቻ መንገድ ሆኖ በመገኘቱ እንደ ሀገር እየተሰራበት ይገኛል።

‎በቤንች-ሸኮ ዞን ባሉ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ትምህርት ቤቶች የምገባ ፕሮግራም ከባለፈው አመት ጀምሮ ተግባራዊ መደረጉን የዞኑ ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ አገኘሁ ወርቁ ገልፀዋል።

‎በዞኑ ወደ 277 ትምህርትቤቶች ሲኖሩ ከዚህ ውስጥ ቅድመ አንደኛ ጀረጃ ትምህርት የሚያስተምሩ 211 ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን አመልክተው በ2017 የትምህርት ዘመን በ126 ትምህርት ቤቶች ላይ የተማሪዎች ምገባ መደረጉን ገልፀዋል።

‎በዘንድሮው አመት በዞኑ ባሉ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች በሁሉም ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የምገባው መርሐ ለማካሄድ እቅድ ተይዞ ወደ ስራ እንደተገባ ተናግረዋል ።

‎በዚህ መሠረት የዘንድሮው አመት የተማሪዎች ምግባ መርሐ-ግብር በሁሉም ትምህርትቤቶች በይፋ ስለመጀመሩ የአማን ትምህርት አንዱ ማሣያ ነው ብለዋል።

‎ለምገባው መርሐ -ግብር እውን መሆን የተማሪ ወላጆች ባላሀብቶች የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲሣተፋ እየተደረገ ነው ያሉት ሀላፊው ትምህርትቤቶችም ከውስጥ ገቢያቸው 20 በመቶ ለዚህ አለማ እንዲያውሉ እንደተደረገም አመልክተዋል።

‎በትምህርት ቤቶች ምግባ መካሄዱ ተማሪዎች ትምህርታቸው ሳያቋርጡ በንቃት እንዲከታቱ ከማድረጉ ባለፈ በስነ-ልቦናም በአካልም ጠንካራ እንዲሆኑ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል ።

‎የሚዛን-አማን ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ደረጀ ኪዊክ በበኩላቸው ባለፈው አመት በሁለተኛው መንፈቅ አመት የተማሪዎች ምገባ መርሐ-ግብሩ መካሄዱን አስታውሰው ምገባውም በ23 ትምህርት ቤቶች መደረጉት ገልፀዋል።

‎በዘንድሮው አመት በ23 ትምህርትቤቶች የምገባው መርሐ-ግብር እንደሚካሄድ እና ዛሬ በአማን ትምህርት ቤት መጀመሩን አመልክተዋል።

‎ምገባው በተማሪዎች መሀከል ይፈጠር የነበረው የአመጋገብ ልዩነት የፈታና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ትምህርት ቤት እንዲመጡ ና እንዲቆዩ በማድርግ የትምህርት ተሳትፎ እንዲያድግ አስተዋፅኦ አድርጓል ብለዋል።

‎በከተማ አስተዳደሩ የአማን ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ፎታ የተማሪዎች ምገባ መጀመሩ ለትምህርት ስራው አጋዥ ስለሆነ ለምገባው ስራ በቀበሌው የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማወያየት እየተሰራ ያለው ስራ ውጤታማ እንደሆነ ተናግረዋል።

‎የአማን የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ር/መ ከድር ሀምዛ በበኩላቸው ባለፈው አመት በትምህርት ቤቱ ምገባ ከ215 በላይ ተማሪዎች መገልገላቸውን አመልክተው መርሐ-ግብሩ መካሄዱ ተማሪዎች በሰአት እንዲመጡ ከማድርግ ባፋለ በተማሪዎች ስነልቦና ላይ ይደረስ የነበረውን ጫና እንዲቀንስ አድርጓል ብለዋል።

‎በምገባ ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የዞኑ ትምህርት መምሪያ አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የመማሪያ ቁሣቁስ ድጋፍ መደረጉን ቤንች ሸኮ ቴቪ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *