




የፀጥታ ምክር ቤት ውይይቱን የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን እና የቤንች ሸኮ ዞን ሰላምና ፀጥታ ሚሊሻ መምሪያ ሀላፊ አቶ ዘማች በዛብህ እየመሩ ይገኛል።
በዞኑ በሰላምና በፀጥታ በሁሉም ዘርፍ በ2017 በጀት አመት የላቀ ስራ መሰራቱን የገለፁት የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን ዞኑ በተጠናቀቀው በጀት አመት ፍፁም ሰላም መሆኑን ጠቅሰው የዞኑን ሰላም ዘላቂ እንዲሆን የሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት እንደሆነ ገልፀዋል።
የዞኑ ሰላም አስተማማኝ በሆነ መንገድ ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ተግባራዊ አቅጣጫዎችንና የጋራ የአፈፃፀም ስልቶችን በማስቀመጥ በየወቅቱ በመገምገም አመርቂ ውጤት መምጣቱንም አስተዳዳሪው አውስተዋል።
የዞኑ ሰላም ፀጥታና ሚሊሻ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘማች በዛብህ በዞኑ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ ከምንጊዜውም በላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተስራ እንደሆነ ተናግረዋል።
በመድረኩ ወቅታዊ ዞናዊ የፀጥታ ግምገማና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የተዘጋጀ ሰነድ የዞኑ ሰላም ፀጥታና ሚሊሻ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘማች በዛብህ እያቀረበ እንደሚገኝ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘግቧለ
በመድረኩ ላይ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን፣ የዞኑ ሰላምና ፀጥታ ሚሊሻ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘማች በዛብህ ጨምሮ የፀጥታ ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።
