


የብልጽግና ፓርቲ 2018 በጀት ዓመት የሩብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ዛሬም ቀጥሎ በመካሄድ ላይ ነው።
በዛሬው መድረክም በፓርቲና በመንግሥት ቅንጅት የሚሰሩ ስራዎች አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት እየተካሄደ ሲሆን የስራ ዕድል ፈጠራ ፣ኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የተሰሩ ስራዎችና የተገኙ ውጤቶች እንዲሁም ከተረጅነት የመላቀቅ ግቦች የውይይቱ አጀንዳዎች ናቸው።
የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ እንዳሉት፤ ኑሮ ውድነትና ስራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት የሚሹ አንገብጋቢ አጀንዳዎች ናቸው።
ከተረጂነት መላቀቅ የተሟላ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መንገድ መሆኑን ገልጸው በዚህ ላይ በተቀናጀ አግባብ መስራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በኑሮ ውድነት ፣ስራ ዕድል ፈጠራና ከተረጅነት የመላቀቅ አገራዊ ግቦች በተሟላ መልኩ እንዲተገበሩ የባለደርሻ ተቋማት ቅንጅት ሊጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በአፈፃፀም ደረጃ እንደ አገር ውጤቶች መገኘታቸውን ጠቁመው ከቦታ ቦታ ያለውን የአፈጻጸም ልዩነነት ለማጥበብ መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል።
በዘርፉ ውጤታማነትን ለማሳደግ በጋራ ማቀድ እና አፈጻጸሞችን በጋራ በጥልቀት እየገመገሙ መሄድ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።
