የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ከክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች ስልጠና እየሰጠ ነዉ።

Spread the love

የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ከብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቅ/ጽ/ቤት ጋር በመተባበር “ከመልካም አመራርነት ወደ ታላቅ አመራርነት መሻገር ” በሚል መርህ ቃል ለክልሉ አመራሮች ያዘጋጀው የአቅም ግንባታ ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል።

በተለዋዋጭ ሁኔታዎች ዉስጥ ፍጥነትና ፈጠራን ማዕከል ያደረገ የአመራር ስርዓት መገንባት የወቅቱ አንገብጋቢ ጉዳይ መኾኑን ነው የክልሉ የብልግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን የገለጹት።

በየጊዜው አመራሩ የወሰዳቸው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የአስተሳሰብና የተግባርአንድነት እንዲፈጠር ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ነው አቶ ፍቅሬ የገለጹት።

የብልፅግና ፓርቲ ሀገራችንን ከውስብስብ ችግር በማውጣት ወደ ብልጽግና ማማ ለማውጣት በሚደረገው እርብርብ የአመራሩን አቅም በመገንባት ከወቅቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ራሱን እያላመደ መምራት እንዲያስችለው የአቅም ግንባታ ስልጠና የማይተካ ሚና እንዳለውም ነው አቶ ፍቅሬ ተናግረዋል።

ስልጠናው ጊዜያዊ ፈተናዎችን ወደ ዕድል የመቀየርአቅም ለመላበስ፣ ዉጤታማ የመሪነት ብቃት ለመፍጠር፣ከተግዳሮት በላይ የሆነ ዕይታ ለማስፋት፣ ህብረ-ብሔራዊ አንድነት ለማጠናከር፣ በአገልጋይ መሪነት ባህሪያት ለመታነጽና ጠንካራ የአመራር ዲሲፕሊን በመገንባት በሀሳብና ተግባር አንድነት የላቀ ድልና ስኬት ለማረጋገጥ በእጅጉ ወሳኝ መኾኑንም አንዲሁ።

ስልጠናውን የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ (AFLEX) ፕሬዚዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ እየሰጡ ይገኛል።

ስልጠናው፥ በወቅታዊ አለም አቀፋዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች እንዲሁም የአመራሩን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለማጎልበት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ክልላዊ እና ሀገራዊ ኃላፊነትን በብቃት የሚወጣ አመራር መፍጠር ላይ ትኩረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደሆነም ተመላክቷል።

ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሚሰጠዉ ስልጠና የክልል ማዕከል ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞን፣ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *