



በጊምቦ ወረዳ ግብርና ደን አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት የግብርና ልማት ሰራተኞች የግምገማ ነክ ስልጠና መድረክ እየተካሄደ ይገኛል::
የግብርናውን ዘርፍ በቴክኖሎጂ በማስደገፍ ውጤታማ መሆን ያስፈልጋል ሲሉ የገለጹት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የግብርና ባለሙያዎች በአርሶ አደሩ ማሳ የተጠናከረ የክትትልና ድጋፍ ስራ በመስራት ምርትና ምርታማነትን ማረጋገጥ አለባቸው ብለዋል::
በወረዳው በሚገኙ ቀበሌዎች የኢንቨስትመን መሬት የወሰዱ ባለሀብቶች በቴክኖሎጂ ማልማትን ለአርሶ አደር ሞዴል መሆን አለባቸው ያሉት የግብርናውን ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ ዞን እና ክልል ጠንካራ የሆነ ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል::
ያሉንን እምቅ አቅሞች ወደተጨባጭ ሀብት ለመቀየር እስካሁን ያሉ ጠንካራ ጎኖችን ማስቀጠል እና ጉድለቶችን ማረም ከዝህ መድረክ በኋላ እንደምጠበቅ አቶ ማስረሻ በላቸው ጠቁመዋል::
ባለፉት ጊዜያቶች የተከናወኑ ተግባራቶችን መነሻ በማድረግ የጽ/ቤትና የቀበሌ ባለሙያዎች ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሂስ ግለ ሂስ መድረክ የሚካሄድ ሲሆን አመለካከት፣ክህሎት፣ተግባር አፈጻጸም፣ሙያዊና ስነምግባር ላይ ያተኮረ ግምገማ የሚደረግ መሆኑ ነው የተገለጸው::
በወረዳዉ ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የአየር ንብረት በመኖሩ በየልማት ጣቢያ የሚገኘው የተማረ የሰዉ ሀይል ጋር በማስተሳሰር በሁሉም የግብርና ዘርፍ ተጠናክረዉ እየተሰራ መሆኑን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ትብብሩ አሰፋ ገልጿል።
በበጀት ዓመቱ ቡናን በክላስተር ለማልማት በፎለር ፕሮግራም በአምስት ቀበሌዎች የጉድጓድ መቆፈሪያና የጉንድላ ማሽኖችን ተደራሽ በማድረግ እየተሰራ ነዉ ያሉት አቶ ትብብሩ አሰፋ ቡና ከካፋ ማህበረሰብ ጋር ያለዉን የኢኮኖሚያዊና ታሪካዊ ትስስርን በመገንዘብ በስፋት ለዓለም ገበያ ለማቅረብ በአጽኖት እየተሰራ ነዉ ማለታቸዉን የዘገበዉ የጊምቦ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ነዉ።
