የፌደራል እና የክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከሰሜን ቤንች ወረዳ ህዝብ ጋር በልማትና በመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ ተወያዩ።

Spread the love

በሰሜን ቤንች ወረዳ ከህዝብ የተወከሉ የፌዴራልና የክልል ምክር ቤት አባላት ከማህበረሰብ ክፍሎች የተወጣጡ የህዝብ ተወካዮች ጋር በልማትና በመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ አካሂዷል።

በህዝቡ ዘንድ አለአግባብ (ህገወጥ)ጥሎሽ ወጣቶችን አላሰፈላጊ ድርጊት ውስጥ እንዲገቡ ያደረጋል ስለዚህ መፈትሔ እንዲያገኝ በፌደራል እና በክልል ደረጃ ህጋዊ ግራውንድ እንዲይዝ ቢደረግ የሚሉና መሰል የመልካም አሰተዳደር ችግሮች በሰፊው ተነስተዋል።

በተጨማሪ የኑሮ ውድነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እየሄደ ያለበት አግባብ ስላለ መንግስት ይህን የኑሮ ውድነት በዘላቂነት እንዲፈታ ከቤንዚን ዋጋ ንረት ጋራ ተያይዞ ያለውን ህገወጥ የንግድ እንቅሰቃሴ ቁጥጥር እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

የተነሱ ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ እንዲፈቱ ከሚመለከታቸው የመንግስት እርከኖች ጋር ጥልቅ ውይይት የሚደረግ መሆኑን የተናገሩት አቶ ካናንስ ታደሴ የህዝብ ተወካዮች አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሹ እስከሚሰጥ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያደርጉም ጠቅሰዋል።

ከህዝብ ከተነሱ ጥያቄዎች የመንገድ ችግር፤ የኤለክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ችግር፤ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ችግር፤ ወጣቶች ኢንቨስትመንት ስራ ዕድል ፈጠራ፣ ትምህርት ጥራት ጉዳይ ፣ በጤና ተደራሽነት እና ሌሎችም የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ተነስተዋል ።

ሌሎች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ምላሽ እንዲያገኙ ከህዝብ የተነሱ መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ናቸው።

በወረዳው ስራ አጥ ወጣቶች ችግሮች ዘላቂ መፈትሔ እንዲያገኙ በፌደራል ደረጃ ፋብሪካ መሰል መሠረት ልማት ስራዎች ለአካባቢው እንዲሰራ አለመደረጉ የአካባቢው ማህበረሰብ በሚያመርተው ምርት ተጠቃሚ እየሆኑ ስላይደለ የሚመለከተው ባለድርሻ አካላት እልባት እንዲያገኝ ቢሰራ የሚል ተነስተዋል።

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል የሆኑት የተከበሩ አቶ ካናንሰ ታደሴ ከህዝቡ የተነሱ መሠረተ ልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች እልባት እንዲያገኙ ጠንካራ ጥረት እናደርጋለን ብለዋል።

በውይይት መድረኩ ከወረዳው ህዝብ የሚነሱ መሰረታዊ የልማት ጥያቄዎች በየደረጃው ባሉ አስፈፃሚ አካላት ምላሽ እንዲያገኙ ልዩ ትኩረት በመስጠት እንደሚሰራ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ክቡር አቶ ካናንሰ ታደሰ ተናግረዋል።

የሰሜን ቤንች ወረዳ ዋና አሰተዳዳሪ አቶ ስንታየሁ በፍቃዱ በውይይቱ እንዳሉት በወረዳ ደረጃ ልፈቱ የሚችሉ መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በአጭር ጊዜ እልባት እንዲያገኙ የወረዳ አስተዳደር ይሰራል ብሏል።

በመድረኩ በፌዴራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ አቶ ካናንስ ታደሰ እና ክብርት ወ/ሮ ኢየሩሳሌም ሌዊ ጨምሮ የክልል ምክርቤት አባል ክብርት ወ/ሮ ቡዝነሽ ሻንቆ፣ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ስንታየሁ በፍቃዱ እንዲሁም የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮች ተሳትፈዋል።

በመጨረሻም የአፈዲሪ እና የክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በበኩላቸዉ በሰሜን ቤንች ወረዳ ከህዝብ የተነሱት የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን ከወረዳ ጀምሮ እስከ ፌዴራል የሚመለከታቸዉ አስፈጻሚ አካላት ምላሽ በመስጠት እንዲፈጽሙት የማድረግና ለተግባራዊነቱ የክትትል ስራ እንደሚሰሩ ገልፀዋል የቤንች ሸኮ ዞን ኮሙኒኬሽን ዘግቧል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *