








የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦቸች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አመራሮችና አባላት በቦንጋ ከተማ የፅዳት ዘመቻ ተካሂዷል።
በመርሀ ግብሩ የክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሰብለጸጋ አየለ እንደገለፁት የዛሬው የጽዳቱ ዋና አላማ የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀ የጽዳት ፕሮግራም መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለነዋሪዎች ውብና የተመቸ አካባቢ መፍጠር የፓርቲው አንዱ ትልቁ ትኩረት መሆኑን አንስተው ብልጽግና በራሱ ሰው ተኮር በመሆኑ ደም በመለገስ፣ አካባቢን በማጽዳት እየተከበረ ይገኛል ብለዋል።
ወ/ሮ ሰብለጸጋ አክለውም ሰኞ ዕለት የደም ልገሣ ፕሮግራም መኖሩንና በተመሳሳይ በዚህም ደም ልገሣ መርሃ ግብር ሁሉም እንዲሳተፉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
በጽዳት ዘመቻው የክልል፣ የካፋ ዞንና የቦንጋ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አመራሮች ፣ አባላት እና የሴክተር መስሪያ ቤት ባለሙያዎች ተሳታፊዎች ሁነዋል፡፡
በተከተል ወ/ሚካኤል
