
“ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ናት። ኢትዮጵያ ከፍተኛ ኢኮኖሚ፣ የሕዝብ ብዛት እና የዘመነ ሰራዊት ያላት ሀገር ናት። የማንሰራራት ጉዟችን እንዳይስተጓጎል ከሁሉም ጎረቤቶቻችን ጋር በሰላም መኖር እንፈልጋለን። ባለፉት ሰባት ዓመታት አንድም ግጭት ከጎረቤት ሀገራት ጋር አላደረግንም። በትብብር አብሮ ማደግ ነው ፍላጎታችን። ሰላማችንን የሚያሰጋ ነገር ካለ ግን ኢትዮጵያ ራሷን ለመከላከል በቂ አቅም አላት። ኢትዮጵያን ለማበልፀግና ለማጽናት የሚያበቃ በቂ አቅም አለን።“ ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
