የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የጋራ ፎረም ተሳታፊ አፈጉባኤዎች በቦንጋ ከተማ የሚገኙ የልማት ስራዎችንና ታሪካዊ ቦታዎችን እየጎበኙ ነው

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የተዘጋጀው የክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የአፈጉባኤዎች የጋራ ፎረም ተሳታፊ አፈጉባኤዎች በቦንጋ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችንና ታሪካዊ ቦታዎች ጉብኝት በማድረግ ተጀምሯል።

በፎረሙ ላይ ከክልሎችና ከሁሉቱም ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የምክር ቤቶች አፈጉባኤዎች እየተሳተፉ ሲሆን በዛሬው እለትም በቦንጋ ከተማ የሚገኘውን ጥንታዊ የካፋ ነገስታት መናገሻ ስፍራ የሆነውን ቦንጌ ሸምባቶ እየጎበኙ ሲሆን በመቀጠል የቦንጋ ዩኒቨርሲት የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተዟዙረው የሚጎበኙም ይሆናል።

ጉብኝቱ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ገልጸው በጉብኝታቸውም ምክር ቤቶቹ በጋራ መመካከር፣ ለጋራ ጥቅም አብሮ መስራት እና አብሮ የመኖር የመቻቻል እሴቶችን ከማሳደግ ረገድ የክልሎች ምክር ቤት የሚጫወቱት ሚና የጎላ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በፎረሙ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ክቡር አቶ ወንድሙ ኩርታ የክልል ምክር ቤቶች በህዝቦች መካከል የመቻቻል እና አብሮ የመኖር እሴቶችን ማጎልበትና ማብቃት ተልዕኮቻቸውን የመፈጸም አቅም የሚያሳድጉበት መሆኑም ገልፀዋል፡፡

በተከተል ወ/ ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *