ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እና የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ በምዕራብ ኦሞ ዞን እየተሠሩ ያሉ የፀጥታ ሥራዎችን ገመገሙ

Spread the love

ከዞኑ ከተለያዩ ወረዳዎች ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በተደረገው ውይይት መድረክ እስካሁን በዞኑ ከፌደራል ጀምሮ የነበረው የፀጥታ አካላትና አመራሩ ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት በተሠራው ሥራ የተሻለ ሠላም በአከባቢው እየመጣ መሆኑን ተሳታፊዎች አንስተው የተጀመረው ሥራ ተጠናክረው እንድቀጥልና ዘላቂነት ሠላም ማረጋገጥ እንድሠራ አሳስበዋል::

ከዚህም ባሻገር በአከባቢው ለፀጥታ ስጋት የሚሆኑ ጉዳዮችን ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት መፍታትና የመከላከያ ሠራዊት ድንበር አከባቢ ጥበቃ በማድረግ ከውጭ የሚሰነዘር ጥቃት መከላከል ላይ ድጋፍ እንዲደረግ አንስተዋል::

በመድረኩ ላይ የተገኙት ሌተናል ጀነራል አስራት ደነሮ በዞኑ ሲሰሩ የነበሩና የተገኙ ውጤቶችን በዝርዝር አንስተው ቀጣይ ቀሪ ሥራዎች ላይ አመራሩ፣ ህዝቡና የፀጥታ መዋቅር በማጠናከር አሁን የተገኘውን ውጤት ማላቅ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል::

የማዕአላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ በቀጠናው በቀጣይነት በትኩረት እንደሚሠራ አንስተው የውስጥ ችግሮችን በተጀመረው አግባብ መፍታት ተገቢ መሆኑን አስመረው ተናግረዋል::

ከዚህም ባሻገር የህገ ወጥ ጦር መሳሪያ ቁጥጥር ያለምህረት ልሠራ እንደሚገባም በትኩረት አንስቷል:

: ጀነራል መኮንኑ አያይዘው ድንበር በመጠበቅም ህብረተሰቡ እንደወትሮ ሁሉ በተደራጀ መንገድ የድንበር ጠባቂነት ታሪካዊ ሀላፊነታችሁን መወጣት የሚገባ መሆኑን አስረድቷል::

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ከፌደራል እስከ ወረዳ ያለው የፀጥታ አካላትና አመራሩ በመቀናጀት በዞኑ የመጣው ሠላም ትልቅ ውጤት መሆኑን አንስተው በሂደቱ የተሳተፉና የድርሻቸውን የተወጡ አካላትን አመስግነዋል::

ርዕሰ መስተዳድሩ እስካሁን የመጣው ውጤት ለማዝለቅ የህግ ማስከበር ሥራ ተጠናክሮ እንድሰራ፣ የህገ ወጥ ጦር መሣሪያ ምዝገባና ቁጥጥር እንድጠናከር፣በማዕድን አካባቢና በወረዳዎች መካከል በወሰን አካባቢ የሚስተዋሉ ችግሮችን በወንድማማችነት እና በመተጋገዝ መንፈስ ለቅመው መፍታትና ሌሎች የውስጥ ችግሮች በየደረጃው ያሉ አመራር;የፀጥታ አካላትና ህዝቡ በመቀናጀት መፈታት እንደሚገባ አንስተዋል::

ርዕሰ መስተዳድሩ ዞኑን ከፀጥታ ስጋትነት አውጥተን የብልፅግና ማዕከል ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች በተቀመጠው አግባብ ተጠናክረው እንዲቀጥል አመራሩና የፀጥታ መዋቅሩ ለውጤታማነት መትጋት እንደሚገባ ዝርዝር የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *