በፓርቲያችን መሪነት ጠንካራ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል ፦አቶ ነጋ አበራ

Spread the love

በፓርቲያችን ብልጽግና መሪነት የተደራጀ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ውጤታማ ስራዎች መመዝገቡን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ ገለጹ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ የ2017 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡

በመድረኩ መክፈቻ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ እንደገለጹት ፓርቲያችን ብልጽግና የትዉልድ ፓርቲ አንደመሆኑ የአስተሳሰብ ልዕልናን በማረጋገጥ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ዕውን ለማድረግ በርካታ ውጤታማ ሥራዎችን ፈጽመዋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተናበበና ውጤታማ ሰፋፊ የፖለቲካና የልማት ስራዎችን በመስራት ለሁለንተናዊ ብልጽግና መሰረት የሚጥል ውጤቶች መመዝገቡን ገልጸዋል።

በዚህም ዘላቂና አዎንታዊ ሰላም ለማረጋገጥ፤ ከተረጂነትና ልመና አስተሳሰብ ለመላቀቅ ፣በክህሎት መር ስራ ዕድል ፈጠራ ፣የኑሮ ውድነትን ለማቅለል በተሰራው አመለካከት ግንባታ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት የታየበት አዎንታዊ የአስተሳሰብና ተግባር አንድነት ለመፍጠር ተችሏል።

በተለያዩ ጊዜያት ለአመራርና አባል የተሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና በፈጠረው ዕይታ ለውጥ ቁጭትን፣ መነሳሳትንና የስራ ትጋትን ከመፍጠር ባሻገር በፓርቲ መሪነት የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ፣ የሌማት ትሩፋት፣ የበጋ ስንዴ ልማትን ጨምሮ ሌሎች ተግባራትን

በየደረጃው ያሉ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮችና አባላት በግንባር ቀደምትነት አርዓያ ሆነው በመፈፀምና በማስተባበር በርካታ ድሎችን ማስመዝገብ እንደተቻለ አብራርተዋል።

በመድረኩ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች፣የዞን የወረዳ/የከተማ አስተዳድር የዘርፉ አመራሮች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *