





በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ሀብት አፈራለሁ፤ የሀገሬን ብልጽግና፤ እጠብቃለሁ ፣የኢትዮጵያን ብልጽግና አፋጥናለው ” በሚል መሪ ሀሳብ በቦንጋ ከተማ ከወጣቶች ሊግ አባላትና ደጋፊዎች ጋር ውይይት ማካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩ ወጣቶች ሀብት መፍጠር ፤መጠቀም እና ማስተዳደር ፣ዘላቂ ሰላም ማስፈን ፤ ብሔራዊ መግባባት እና ጠንካራ ሀገርን በመገንባት የወጣቶች ሚና፣ ገዢ ሀገራዊ ትርክትና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ትኩረት ያደረገ ውይይት እየተካሄ ነው።
በአሁኑ ሰአት የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል በሆኑት በወጣት ፍቀዱ ሀጢያ ሰነድ እየቀረበ ይገኛል።
በውይይት መድረኩ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ሥራ አስፈፃሚ አባላት፣ የክልል አመራሮች፣ የከተማ የሊጉ አባላት እና ደጋፊዎች ተገኝተዋል።
