የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ ለመፍጠር በሚደረገዉ ርብርብ የግል ኮሌጆች ሚናቸዉን በግባቡ ሊወጡ ይገባል፦አቶ ተስፋዬ እንዳሻዉ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ከግል ኮሌጆች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በቦንጋ ከተማ የምክክር መድረክ አካሄደ።

የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ እንዳሻዉ በመክፈቻ ንግግራቸዉ ብቁ የሆኑ ዜጎችን ለመፍጠር የግል ኮሌጆች ሚናቸዉ የጓላ መሆኑን ገልጸው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በሚደረገዉ ርብርብ የግል ኮሌጆች ሚናቸዉን በአግባቡ መወጣት አለባቸዉ ብለዋል።

እያንዳንዳቸዉ ኮሌጆች በመማር ማስተማር ሂደት ላይ ምን ደረጃ እንዳሉ ለማወቅ ኦዲት መደረግ እንዳለበት የተናገሩት ኃላፊው በሀገራችን ወቅቱን በጠበቀ መልኩ ኮሌጆች ስታንዳርዱን ጠብቀዉ ብቃት ያለውና ተወዳዳሪ የሰዉ ሀይል መፍጠር አለባቸው ብለዋል።

የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ ወ/ ሮ ቤተልሔም ዳንኤል በበኩላቸዉ በክልላችን በሚገኙት የግል ኮሌጆች ላይ ያተኮረ ኦዲት ማድረግ አሰፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

በመድረኩ የግል ኮሌጆችን ኦዲት ሪፖርት ያቀረቡት የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ካሳሁን በበኩላቸው ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ኮሌጆች በተቀመጠው የመማር ማስተመር መመሪያ መሰረት ትዉልድ የመቅረጽ ኃላፊነት እንዳለባቸዉ ገልጸዋል።

በመሆኑም እያንዳንዳቸዉ ኮሌጆች በተቀመጠዉ ስታንዳርድ መሰረት ተግባራዊነታቸዉን በመለየት መበረታታት ያለበትን ተቋም ቴክኒክና ሙያ እንዲደግፍ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መደረጉን የገለጹት አቶ ለገሠ በኦዲት ግኝቱ ስታንዳርዱን ያላሟሉ 11 ኮሌጆች የተሰረዙ ሲሆን ዘጠኙ ደግሞ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በፀሀይ በላቸው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *