የኪ-ጥበብ ባለሙያዎች አሰባሳቢ ትርክት በመፈጠርና በማስረጽ ረገድ የጎላ አበርክቶ አላቸው፦ አቶ ማስረሻ በላቸው

Spread the love

“ሀገር እና ጥበብ፤ ጥበብ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት!” በሚል መርህ ቃል ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የተዘጋጀ ክልላዊ የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፥ የኪ-ጥበብ ባለሙያዎች አሰባሳቢ ትርክት በመፈጠርና በማስረጽ ረገድ የጎላ አበርክተው እንዳላቸው ተናግረዋል።

ኪነ-ጥበብ በሀገር ግንባታ፣ ታሪክና ትርክት እንዲሁም የማህበረሰብ ልማድና ዕሴት ከትውልድ ወደ ትውልድ በማሸጋገር እንዲሁም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትና ዕድገት በመደገፍ የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለውም ነው አቶ ማስረሻ የገለጹት።

የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በጥበብ ስራዎቻቸው ውስጥ የማህበረሰብ የጋራ ዕሴት፣ ወግና ባህልን በማንጸባረቅ ማህበረሰባዊ አንድነትን የሚፈጠሩ እንደሆነም ነው የጠቆሙት።

በሀገራችን ኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ ታሪክ ውስጥ የኪነ-ጥበብ አሻራ ደማቅ እንደነበረ የገለጹት አቶ ማስረሻ ይሁን እንጅ የድህረ-እውነት ዓለም በፈጠረው አጋጣሚ ከዚህ አውንታዊ አበርክተው በተቃራኒው የተሰለፉ እንዲሉም ነው የገለጹት።

በመሆኑም የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች አውንታዊ አበርክቷቸውን በማጠናከር በሀገር ግንባታ ውስጥ የሚጫወቱትን ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉ አቶ ማስረሻ ጠይቀዋል።

ከክልሉ ምሥረታ ወቅት ጀምሮ፤ በክልሉ የሚገኙ የኪ-ጥበብ ባለሙያዎች በልዩነት ውስጥ ያለውን አንድነት በማጉላት፣ ብሄራዊነትንና ክልላዊ አንድነትን በመፈጠር ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክልሉ መንግሥት እውቅና እንደሚሰጥ የገለጹት አቶ ማስረሻ ዘርፉውን በመደገፍ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት የክልሉ መንግሥት ዝግጁ መኾኑን ተናግረዋል።

የክልሉ የባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ በበኩላቸው የክልሉ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፥ ክልላዊ አንድነትን በስራዎቻቸው በማጠናከር ለክልላዊ ስነ-ልቦና ግንባታ እየተወጡ ላለው አበርክተው ምስጋና አቅረበዋል።

አቶ ፋንታሁን ዝርዝር የመወያያ ስነድ እያቀረቡ የሚገኙ ሲሆን፥ በቀረበው ስነድ መነሻ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *