




ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጽያ ህዝቦች ክልል ከሁሉም አከባቢዎች የተወጣጡ የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ አመራሮች እና ባለሙያዎች እንዲሁም የኪነጥበብ ባለሙያዎች በቦንጋ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል።
የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የኪነጥበብ ባለሙያዎች በቦንጋ ከተማ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ ከሚገኘው ገቢ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እየተገነባ የሚገኘውን የመደመር ትውልድ የቤተ መጽሐፍት ግንባታ ምልከታ አድርገዋል።
በቦንጋ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የመደመር ትውልድ ቤተመጻሕፍት ፕሮጀክት ግንባታ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) መሠረተ ድንጋይ ተቀምጠው ወደ ተግባር የተገባ ነዉ።
በተሻለ ፍጥነት እየተሰራ የሚገኘዉ የመደመር ትውልድ ቤተመጽሐፍት ፕሮጀክት ግንባታ አፈጻጸም አሁን ላይ 95 ከመቶ የደረሰ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ተመርቀዉ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እና በርዕሰ መስተዳድር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ቅርብ ክትትል የተገነባው የቦንጋ ከተማ ኮሪደር ልማት አካል የሆነው የአረንጓዴ ፓርክ የምልከታዉ አካል ነዉ።
በምልከታዉ የክልሉ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ አመራሮች እና ባለሙያዎች እንዲሁም የኪነጥበብ ባለሙያዎች ተሳታፊዎች ናቸዉ።
በፍቅር ከበደ
