





“ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በተለያዩ ኩነቶች መከበሩም ተገልጿል።
ቀኑን በማስመልከት በሚዛን አማን ከተማ የማጠቃለያ ውይይትም ተካሂዷል።
በውይይት መድረኩ የዴሞክራሲና የፌዴራል ስርአት በኢትዮጵያ ተስፋዎች እና ተግዳሮቶችን የሚዳስስ የውይይት መነሻ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
በውይይት መድረኩ አንዳንድ ተሳታፊዎች ሰጡት አስተያየት ክልሉ የተፈጥሮ ሀብት ፀጋ ባለቤት እና የሰላም ተምሳሌት እንደመሆኗ ሰላሟንና አንድነቷን ለማስጠበቅ እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
ለዴሞክራሲ ስርዓት መጎልበት በጋራ እንደሚሰሩ የተናገሩት የውይይቱ ተሳታፊዎች አብሮነትን፣ አንድነትን እና የወንድማማችነት መንፈስን ለማጠናከር የበዓሉ መከበር ሚናው የጎላ መሆኑን ነው የተናገሩት።
ተሳታፊዎቹ ከዚህ ቀደም የነበሩ የተሳሳቱ ትርክቶችን በማረም ለዴሞክራሲ ስርዓት መጎልበትና ለብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የጋራ ትስስርና አንድነት አስተዋፅኦ ለማበርከት እንደሚተጉም አረጋግጠዋል።
በመድረኩም በፌደራሊዝም ላይ ያተኮረ የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር የተካሄደ ሲሆን በውድድሩም የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
ሁሉም ዞኖች ከትምህርት ቤቶች ጀምሮ በዓሉ እንዲከበር ላበረከቱት አስተዋፅኦ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።
20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ ኅዳር 29 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ይከበራል።
በካሳሁን አሰፋ
