




መንግሥት በሕዝባዊ ተሳትፎ ሀገራዊ የልማት ኢኒሼትቮችን በማፋጠንና ነባር ተግዳሮቶችን ወደ እድል በመቀየር የዜጎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ እያደረገ ይገኛል፡፡
የሕዝብ የነቃ ተሳትፎ በመላ ሀገሪቱ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ኢኒሼቲቮችን ለመደገፍ ከፍተኛ አቅም እንዲፈጠር ያደረገ በመሆኑ አካታች እድገትን እና ፍትሐዊ የሀብት አጠቃቀም እዉን እንዲሆን አድርጓል፡፡
የህዝብ የልማት ተሳትፎ በመንግሥት እና በሕዝብ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር፣ ሀገሪቱ በመሠረተ ልማት፣ በማህበራዊ አገልግሎቶች እና በኢኮኖሚያዊ ሽግግር ሂደት ዉስጥ አካታች እድገት እንዲረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባና ስልጤ ዞኖች፣ እንዲሁም በምስራቅ ጉራጌ ቡታጅራ ከተማ ዉስጥ እየተሰሩ ያሉ የልማት እንቅስቃሴዎችን ከክልሉ አመራሮች ጋር ተዘዋዉረው ምልከታ አድርገዋል ፡፡
በሁሉም አከባቢዎች ጸጋዎችን በመለየት ወደ ሀብት ለመቀየር በተሰሩ የልማት ኢኒሼቲቭ ሥራዎች በርካታ ውጤች የተመዘገቡ ሲሆን የሕዝብ ተሳትፎ የልማት ስራዎችን በማገዝ ረገድ ትልቅ አቅም እንዳለው ጠቁመዋል ።
ሚነስትር ዴኤታው በተለይም የሀላባ ሁለገብ ስትደዮም ግንባታና የዉስጥ ለዉስጥ መንገድ ስራዎች፣ እንዲሁም በስልጤ ዞንና ምስራቅ ጉራጌ ቡታጅራ ከተማ እየተሰሩ ያሉ የገጠር ኮሪደር ልማት፣ የኢንዱስትሪ መንደር፣ የወንዝ ዳርቻ እና የመንገድ ግንባታ ስራዎች ህዝቡ በንቃት እየተሳተፈበት በመሆኑ ህዝብ ሲተባበር ምን ያህል ትላልቅ ፕሮጀክቶችን እዉን ማድረግ እንደሚንችል ያሳየ ነዉ ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት በደረገችው ጥረት በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልቅ ተስፋ የታየበት ሥራ አከናውናለች ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዉ፣ ከዚህ አንጻር የተጀመሩ የልማት ኢኒሼቲቮችን ማስቀጠል የሁሉም ዜጎች ድርሻ መሆኑን አንስተዋል ፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በተግባር የሚታዩ የልማት ስራዎች ለሌሎች አከባቢዎች በምሳሌነት የሚወሰዱ ናቸዉ ያሉ ሲሆን፣ በሁሉም የልማት መስኮች ብዙ አስቻይ ሁኔታዎችን አሻግረን በማየት፣ የተሻለ መስራት እንደሚጠበቅ አብራርተዋል ፡፡
መረጃው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ነው።
