በቦንጋ ማዕከል “የህልም ጉልበት፤ለእመርታዊ ዕድገት “!በሚል መሪ ሀሳብ እየሰለጠኑ የሚገኙ የ3ኛው ዙር የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በቦንጋ ከተማ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።

Spread the love

የ3ኛው ዙር ሰልጣኞች በካፋ ቦንጋ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙትን የኮሪደር ልማት ፤ብሔራዊ የቡና ሙዚየም እና የወጣቶች ክላስተር ማዕከላትን እንድሁም የተለያዩ የልማት ስራዎችን በቡድን ተከፋፍሎ ጉብኝት እያካሄዱ ይገኛል።

የመስክ ምልከታዉ ሠልጣኞች ከንድፈ ሀሳብ ባሻገር የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በማምጣት ከተሞክሮና ከልምድ እርስ በርስ እንዲማማሩ የሚያስችል ነው ተብሏል።

የከተማ ኮሪደር ልማት ሥራና ተያያዥ ጉዳዮችን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በተመለከተ የቦንጋ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ስዩም ወ/ሚካኤልና እንደዚሁም የከተማ ማዘጋጃ ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ በረከት ወልዴ ለጎብኚዎች ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥቷል።

አመራሩ በሰጡት ማብራሪያ በኮሪደር ልማቱ ከተሞችን ለኑሮና ለስራ የተመቹ ዘመናዊ፤ ጽዱና ውብ ለማድረግ እየተደረገ ያለው ርብርብም ፓርቲያችንን ዘመኑን የዋጀ የከተማ ልማት ተግባራትን በብቃት የሚተገብር ፓርቲ ነው ለማለት የሚያስችል ነው ብሏል።

የበንጋ ከተማ የኮሪደር ልማት 24 ሰዓታትን በመስራትና ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር ለመኖር ምቹ ማድረግ፣ ማደስና ገጽታዋን በማሻሻል ረገድ የኮረደር ልማት ስራው በመፋጠን ላይ ይገኛል ፡

የቦንጋ ከተማ የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ሥራው የመሠረተ ልማት አውታሮችን በማስተሳሰር ተሰርቶ በሰልጣኞች ጉብኝት የተደረገ ሲሆን በቀጣይ ጊዜያት ቀሪ የኮሪደር ልማት የሚሰራባቸው የከተማዋ አካባቢዎች እንዳሉም ማብራሪያው ተሰጥቷል።

እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር እና መሰል የልማት ተግባራት በርካታ ስራ አጥ ወጣቶችን በዘርፉ በመሰማራት ተጠቃሚ እያደረጋቸው ይገኛል።

እንደ ሀገር የተጀመረውን የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብርን ማሳለጥ የሚያስችል የወተት ሀብት ልማት መንደርም በሰልጣኞቹ ጉብኝት ተደርገዋል።

በአመራሩ ዘንድ የልምድ ልውውጥ መከናወኑ በየአካባቢው ተመሳሳይ የልማት አቅሞችን ለመፍጠር አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑን በጉብኝቱ ከተሳተፉት አመራሮች መካከል አንዳንዶች አስተያየት ሰጥቷልየካፋ ሲል የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *