


በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የተመራው የልኡካን ቡድን ቤይጂንግ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ ሲደርስ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው አቀባበል አድርገውለታል።
ልዑካን ቡድኑ የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነትን ለማጠናከር ያለመ ሲሆን በቆይታውም የሁለትዮሽ ውይይቶች፣ የተሞክሮ ልውውጦች እና የመስክ ጉብኝቶች በተለይም የወደፊት የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነቶችን የሚያጠናክሩ ስትራቴጂያዊ አጋርነት መመስረትን ዓላማ ያደረገ ቆይታ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
