



በምዕራብ ኦሞ ዞን የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የጀሙ የስልጠና ማዕከል ስልጠኞች የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጉብኝት እያካሄዱ ይገኛል።
የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት’በሚል መሪ ሀሳብ እየተሰጠ በሚገኘው ሦስተኛ ዙር ሀገራዊ ስልጠና በምዕራብ ኦሞ ዞን በጀሙ ማዕከል እና በማጂ ማዕከል እየተደረገ ይገኛል።
የመስክ ምልከታዉ ሠልጣኞች ከንድፈ ሀሳብ ባሻገር ከተግባር ተሞክሮና ከልምድ መማማር የሚያስችል እና ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን ለማጠናከር ፋይዳዉ ጉልህ መሆኑ ተጠቁሟል።
ሰልጣኞቹ በምዕራብ ኦሞ ዞን በጀሙ ከተማ እና በመኤኒት ሻሻ ወረዳ የተለያዩ ልማቶችን አየጎበኙ ይገኛሉ።
ሰልጣኞቹ በጀሙ ከተማ ወጣቶች ተደራጅተው እያረቡ ያሉት የዶሮ እርባታ የሊዝ መንደር ለወጣቶች ሥራ እድል ፈጠራ እየተገነባ ያሉት ሼዴዎች በወጣው ሃይሎም እየተሰራ ያለው በ8ወራት እና በ4ወራት የሚደርስ የፓፓያ ምርት እና ሌሎች የምግቤ በጎሮ እና የወጣቶች የእንጨት እና ብረታብረት ሥራዎች እና ሌሎችም ተዘዋውሮ እየተመለከቱት ይገኛል።
