ክልላዊ የገጠር መሬት ባለይዞታዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነዉ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ክልላዊ የገጠር መሬት ባለይዞታዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ የንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የንቅናቄ መድረኩ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን እና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩ የክልሉ ግብርና ቢሮ ከኢፌዲሪ ግብርና ሚኒስቴር በጋራ ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን ”ዲጂታል ማንነት ለተረጋገጠ የይዞታ ባለቤትነትና ለላቀ የፋይናንስ ተጠቃሚነት’ በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

በመድረኩ የፌደራል፣ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *