የግብርና አገልግሎቶችን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ማስተሳሰር የአርሶና አርብቶ አደሮች ሁሉዓቀፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያስችላል ፦አቶ ማስረሻ በላቸዉ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የገጠር መሬት ባለይዞታዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ የንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩ የክልሉ ግብርና ቢሮ ከኢፌዲሪ ግብርና ሚኒስቴር በጋራ ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን ”ዲጂታል ማንነት ለተረጋገጠ የይዞታ ባለቤትነትና ለላቀ የፋይናንስ ተጠቃሚነት’ በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

በንቅናቄ መድረኩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ እንደተናገሩት፤ የግብርና ትራንሰፎርሜሽን እውን ለማድረግ የዘመነና ዲጂታላይዝድ የግብርና አገልግሎቶችን ለአርሶና አርብቶ አደር መስጠት ስንችል ነዉ።

የግብርና አገልግሎቶችን ከዲጂታል ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ማስተሳሰር ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነው አቶ ማስራሻ በላቸዉ የገለጹት።

የሀገራችን አርሶና አርብቶ አደሮች ሰፊ ሀብት እያላቸው ሰርተው የኢኮኖሚ ምንጭ እየሆኑ ነገር ግን ሀገሪቱ ከሚታመጨው ኢኮኖሚ ላይ የፋይናንስ የብድር አገልግሎት ሳይሆኑ መቆየታቸውም አስረድተዋል።

ይህንን ችግር መቅረፍ የሚያስችል በተለይም የግብርና አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝድ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ አርሶና አርብቶ አደሩ ባለው ሀሴት ላይ ተመስርተው የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ስራ እየተከናወነ ይገኛል ነው ያሉት አቶ ማሽረሻ በላቸው።

የአርሶና አርብቶ አደሩ ዋነኛ ሀብቱ መሬቱ ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህም የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ልኬት በሀገር ብሎም በክልሉ በሰፊው እተከናወነ ስለመሆኑንም ጠቅሰዋል።

የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ልኬት ከሀገራዊ መረጃ ሥርዓት ጋር በማቆራኘት ከድጂታል መታወቂያ ጋር በማስተሳሰር ለአርሶና አርብቶ አደሩ የፋይናንስ ተደራሽነት እንዲረጋገጥና የፋይናንስ አቅርቦት ለማሳለጥ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

እንደሀገር ከ12 ሚሊዮን በላይ አርሶና አርብቶ አደር የዲጂታል መታወቂያ እንዲይዝ እንዲሁም በክልላችን 1.99 ሚሊዮን ህብረተሰብ ክፍል የድጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ እንዲሆን በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንዳለም ጠቁመዋል።

ከዚህም ውስጥ ከ398 ሺህ በላይ አርሶና አርብቶ የህብረተሰብ ክፍሎች የዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከተፋሰስ ልማት ግን ለጎን እየተሰራ ይገኛልም ብለዋል።

ይህን ስራ ከሁለተኛ ደረጃ የመሬት ልኬት ጋር በማቆራኘት የብድር አቅርቦት እንዲያገኙ ለማስቻል ከብሔራዊ መረጃ ስርዓት ጋር የብሔራዊ ፋይናንስ አገልግሎት ጋር እንዲታሰር በማድረግ የሁለተኛ ደረጃ መሬት ልኬት እስካሁን ባለው ከ364 ሺህ በላይ ማሳ በክልሉ የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ልኬት ተከናውኗልም ብለዋል።

የግብርና አገልግሎቶችን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ማስተሳሰር የአርሶና አርብቶ አደሮች ሁሉዓቀፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ነው አቶ ማስረሻ በላቸዉ የተናገሩት።

በመድረኩ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን እና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ ጨምሮ የፌደራል፣ ክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *