የምርጫው ውጤት በአዲስ ቁርጠኝነት ለሥራ እንድንነሳሳ የሚያበረታታን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

Spread the love

የምርጫው ውጤት የተጣለብን አመኔታ እና ኃላፊነት በአዲስ ቁርጠኝነት ለሥራ እንድንነሳሳ የሚያበረታታን ነው ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትእና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የፓርቲው ፕሬዚዳንት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ ዛሬ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የብልፅግና ፓርቲን ምርጫ አካሂደናል ብለዋል።

ይኽም ወደ ዲጂታል ሽግግር የምናደርገው የሀገራዊ ጉዞ አካል ነው ሲሉም ገልጸዋል።

በምርጫው ውጤት በእኔና በምክትል ፕሬዝዳንቶች የተጣለብን አመኔታ እና ኃላፊነት በአዲስ ቁርጠኝነት ለሥራ እንድንነሳሳ የሚያበረታታን ነውም ብለዋል።

ሦስተኛ ቀኑን የያዘው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ከፍተኛ በሆነ ድምጽ የፓርቲው ፕሬዚዳንት አድርጎ የመረጠ ሲሆን አቶ ተመስገን ጥሩነህን እና አቶ አደም ፋራህን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንቶች አድርጎ መርጧቸዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *