‹የኢትዮጵያን የልዕልና ጉዞ እናሳካዋለን።

Spread the love

ብልፅግና ፓርቲ የጠራ ሀሳቡንና ትክክለኛ ፖሊሲዎቹን በትጉህ አመራርና አባላቱ በመፈጸም በአስደማሚ ድሎች ጉዞውን ቀጥሏል።

ፓርቲያችን ከእነዚህ ድሎች ማግስት ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ሀገርና ህዝብን እንድናገለግል አደራ ተሰጥቶናል።

በዚሁ መሠረት እኛም የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ እና የህዝባችንን መሻት ለማሳካት ቃላችንን በድጋሚ አድሰናል።

ሁለንተናዊ ክብርና ብልፅግናን የተቀዳጀች ኢትዮጵያን ለትውልዱ ለማስረከብ ለፈተናዎች ሸብረክ ሳንል ያለ እረፍት እንደምንሠራ ለመላው ህዝባችን ማረጋገጥ እፈልጋለሁ።››- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *