




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣ በኮንታ ዞን ኮይሻ ወረዳ ከ142 ሚሊዮን ብር ላይ በጀት የተገነቡ የመንገድ እና የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን መርቀው ከፍተዋል።
በክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ “የገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም” ትብብር በኮንታ ዞን፣ ኮይሻ ወረዳ የተገነባው የደልባ-አልፋ ቶሊቃ የ12.10 ኪሎሜትር መንገድ በአከባቢው ከዚህ በፊት በኅብረተሰቡ የሚነሳውን የመንገድ ችግር የሚፈታ መኾኑ ተመላክቷል።
በኮንታ ኮይሻ ከተማ የነዋሪዎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ጥያቄ በዘላቂነት የሚመልሰው የንጹህ መጠጥ ውሃ ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ሲሆን ፕሮጀክቱ 90 ሚሊዮን ብር የወጣበት እንደሆነና ከ11ሺህ 646 በላይ ነዋሪዎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሚያደርግ የክልሉ ዉሃ፣ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር በየነ በላቸዉ ገልጸዋል።
በምረቃው ስነስርዓት የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የአከባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በዕድገቱ በዛብህ
