




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ግብርና ቢሮ የ2017 የምርት ዘመን የበጋ መስኖ ስንዴ እና መደበኛ መስኖ ዕቅድ ዙሪያ ከዞን፣ ከወረዳና ከባለድሻ አካላት ጋር የንቅናቄ መድክ በቦንጋ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል ።
በንቅናቄው መድረክ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ማስረሻ በላቸው የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ የመድረኩ ዓላማ ከዚህ በፊት ከተመዘገበው ውጤት በመነሳት ለቀጣይ ዝግጅት ከፍተኛ ሚና እንዳለው አሳስበዋል ።
በክልሉ 83 የመስኖ አውታሮች ካሉት ውስጥ 67 አከባቢ በስራ ላይ ሲሆን በነዚህም ወደ 19,000 ሄ/ር ማልማት የሚያስችል መሠረተ ልማት በክልሉ መኖሩን አንስተዋል ።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም የበጋ ስንዴ እንዴ ክልል በ2014 ዓ/ም 433 ሄ/ር የተጀመረውቢሆንም በ2016 ዓ/ም ወደ 5003 ሄ/ር ማድረስ የተቻለና ምርቱንም 149, 953 ኩ/ል ማደረስ የተቻለ እንደሆነና ምርታማነትንም በሄ/ር ከ28.3 ወደ 29.9 ማሳደግ እንደተቻለ አንስተዋል።
በሌማት ትሩፋትም አርሶ አደሩ ከእንስሳት ሀብት ዘርፍ የሚያገኘው ጥቅም ከፍተኛ በመሆኑ በዝርያ ማሻሻል፣ በወተትና ስጋ ምርት፣ በዶሮ፣ በዓሣ ምርት የተሻለ ውጤት የተመዘገበ ቢሆንም ከዚህ በመነሳት በያዝነው ምርት ዘመን ዕቅድን በመከለስ ለተሻለ ውጤት በቅንጅት መሠራት እንዳለበት አንስተዋል ።
ለተሳታፊዎች የ2016 በጀት ዓመት የበጋ መስኖ ስንዴ እና መደበኛ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2017 ዓ.ም ዕቅድ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ የ2017 ምርት ዘመን የመደበኛና የሌማት ትሩፋት ተግባራት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ።
በንቅናቄው መድረክ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፣ የመንግስት ረዳት ተጠሪዎች፣ ቢሮ ኃላፊዎች፣ የሴክተሩ ባለሙያዎች፣ የዞንና የወረዳ አስተዳዳሪዎች፣ የመንግስት ተጠሪዎችና የግብርና ጽ/ቤትና የመምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በጌታሁን ግርማ
