የምዕራብና የደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከመደበኛ በላይ ዝናብ ይኖራቸዋል

Spread the love

ኢንስቲትዩት የወቅት ትንበያ ይፋ ለማድረግ ባዘጋጀው የባለድርሻ አካለት መድረክ የባለፈውን የበጋ ወቅት ትንበያ የገመገመ ሲሆን በጋው በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደተስተዋለባቸውና ይህም ሁኔታ በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው ለሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ ለሚገኙ አርሶ እና አርብቶ አደሮች ምቹ ሁኔታን የፈጠረ እንደነበረ ተገልጿል፡፡

በእለቱ የመጪው በልግ ትንበያ ይፋ የተደረገ ሲሆን በልግ ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል መደበኛና ከመደበኛ በታች፤ የቦረናና ጉጂ ዞኖች፤ የሲዳማ፤ የማዕከላዊና የደቡብ ኢትዮጵያ መደበኛና ከመደበኛ በላይ፤ በሌላ በኩል የደቡብ ትግራይ፤ የምስራቅ አማራ፤ አፋር፤ መካከለኛው እና የምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ መደበኛና ከመደበኛ በታች ዝናብ እንደሚኖር ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል የምዕራብና የደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚኖራቸው የተጠቆመ ሲሆን በተጨማሪም የምዕራብ አማራና የጥቂት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ሰሜናዊ ክፍል አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ዝናብ እንደሚያገኙ በመድረኩ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

እንዲሁም በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከመደበኛው አንፃራዊ መጨመር እንደሚኖረው ገለፃ ተደርጓል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *