ቆይታከእኛጋር!

Spread the love

የዚህ ወር “ቆይታ ከእኛ ጋር” እንግዳችን ፕሮግራም

የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የፈተና አስተዳደር ስርዓትን ከኩረጃ የፀዳ ማድረግ፣ የፈተና አሰጣጥን ማዘመን፣ ጠንክሮ በመማርና በማጥናት በራሱ ውጤት የሚያመጣ ትውልድን ስነ ልቦና መገንባት ወሳኝ መሆኑ ይታወቃል ።

በመሆኑም የተማሪ የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን በማስቀረት ብቁ ተማሪዎችን ወደ ቀጣይ ክፍል ለማሳለፍና እንዲሁም ተማሪውን ከቴክኖሎጂ ጋር በማላመድ ብቁና ተወዳዳሪ ለማድረግ ዘርፌ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

የሀገራዊ የፈተና ዝግጅት፣ ፈተናውን በወረቀትና በበየነ መረብ ለመውሰድ የተዘጋጁ ተማሪዎች ብዛት ፣ ፈተና የሚሰጥባቸው ጣቢያዎች፣ ለፈተናው የአስተባባሪዎች፣ የሱፔርቫይዘሮች እና የፈታኞች ዝግጅትና ምደባ፤

እንዲሁም የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ካለፉት ዓመታት የሚለይበት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የመማር ማስተማርና ምዜና ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ደስታ ገነመ (ዶ/ር) ጋር ቆይታ አደርገናል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን (መ/ኮ)፡ የቆይታ ከእኛ ጋር ፕሮግራም እንግዳ ለመሆን ፍቃደኛ ስለሆኑ ከልብ እናመሰግናለን።

ደስታ ገነመ (ዶ/ር) ፦ እናንተም ስለጋበዛችሁኝ አመሰግናለሁ።

መ/ኮ፦ አጠቃላይ የፈተና ዝግጅት ምን ይመስላል ?

ደስታ ገነመ (ዶ/ር)፦ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን የማጠናቀቂያ ሀገራዊ ፈተና በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት ዘርፌ ብዙ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ወደ ማጠቃለያው ምዕራፍ ደርሷል።

መ/ኮ፦ ፈተናው ለምን ያህል ተማሪዎች ከመቼ ጀምሮ ይሰጣል ?

ደስታ ገነመ (ዶ/ር)፦ የ2017 ዓ/ም ሀገራዊ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ/ም ጀምሮ የሚሰጥ ሲሆን በክልላችን በማህበራዊ ሳይንስ ወ 5174 ሴ 4584 ድ 9758 በተፈጥሮ ሳይንስ ወ 5155 ሴ 4214 ድ 9369 በአጠቃላይ ወንድ 10329 ሴት 8798 ደምር 19127 ተፈታኝ ተማሪዎች ሀገራዊ የ12ኛ ክፍል ፈተና ይወስዳሉ፡፡

መ/ኮ፦ ፈተናው በስንት ጣቢያዎች ይሰጣል?

ደስታ ገነመ ዶ/ር፦ የክልላችን ተማሪዎች በ4 ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች እና በ1 ቴ/ሙ/ኮሌጅ በድምሩ በ5 የፈተና ጣቢያዎች ፈተናውን ይወስዳሉ፡፡

መ/ኮ፦ ተፈታኞቹ በስንት ት/ቤቶች ትምርህታቸውን የተከታተሉ ናቸው?

ደስታ ገነመ (ዶ/ር)፦ ተፈታኞች ከ 171 የመንግስት መደበኛ፣ 3 የግል መደበኛ ፣ 15 የማታ እና ከ 41 የርቀት የትምህርት ተቋማት የተመዘገቡ ናቸው፡፡

በ2017 ዓ/ም ሀገራዊ ፈተና ከሚወስዱት ተማሪዎች ምን ያህሉ በወረቀትና በበየነ መረብ ይፈተናሉ ?

ደስታ ገነመ(ዶ/ር) ፦አጠቃላይ ፈተናውን ከሚወስዱ ተማሪዎች መካከል 2690 ተፈታኞች በበይነ መረብ የሚፈተኑ ሲሆን ቀሪዎቹ በወረቀት የሚፈተኑ ናቸው፡፡

መ/ኮ፦የፈተና አሰጣጥና አስተዳደር ከሌላ ጊዜ የሚለይበት ሂደት ምን ይመስላል ?

ደስታ ገነመ(ዶ/ር) ፦ የ2017 ዓ.ም የፈተና አስተዳደሩ ከቀድሞ የሚለየው በዘንድሮው የትምህርት ተቋማት የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በትምህርት ቤቶቻቸው በትጋት የማብቃት ሥራ እየሰራ መቆየታቸውና በበይነ መረብ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞች ቁጥር ከፍ ማለቱ መቻሉ ነው፡፡

በተጨማሪም የዘንደሮው የፈተና አስፈጻሚ ግብረ ሀይል ተደርጅቶ ወደ ተግባር የገባ ሲሆን ከሰኔ 20/2017 ጀምሮ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎች መግባት የሚጀምሩ ይሆናል።

መ/ኮ፦ የፈተና አስፈጻሚዎች ዝግጅት ምን ይመስላል?

ደስታ ገነመ (ዶ/ር)፦ የፈተና አስፈጻሚዎች፣ ሱፐርቫይዘሮችና ፈታኞች ምልመላም በጊዜ ተከናውኖ ወደ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎትም ተላልፏል፡፡

መ/ኮ፦ የዘንድሮ የፈተና ስርዓቱ ከሌላ ጊዜ የሚለይበት ሁኔታ ካለ?

ደስታ ገነመ (ዶ/ር) ፦ የዘንደሮውን ፣ ውጤት በፈተና ብቻ ጠንክሮ በማጥናት እንደሚመጣ ተማሪዎችን ከማሳመን እንዲሁም በስነልቦና ከማዘጋጀት የተሰራው የድጋፊና ክትትል ስራዎች በተጠናከረ ሁኔታ ዝግጅት መደረጉንም ጨምረው አንስተዋል።

የመ/ኮ ፦በመጨረሻ የሚያስተላፉት መልዕክት ካለ በገልጹ?

ደስታ ገነመ (ዶ/ር)፦ ሁሉም የባለድርሻ አካላት ከኩረጃ የፀዳ ፈተና በመፈተን ለተማሪዎች ውጤት መሳካት ብሎም ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ አስፈላጊው ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪውን አቀርበዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *