በጎነት እንደ ባህል

Spread the love

ሪፖርታዥ

በጎነት እንደ ባህል
በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ እያለ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መጀመር እጅግ ጠቃሚ መሆኑ ይነገራል። በጎ ፈቃደኝነት ወጣቶች በተጨባጭ ተግዳሮቶች ውስጥ እንዲሰሩ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ለውጦችን እንዲያደርጉ እድል እንደሚሰጥም ይታመናል። በጎ ፈቃደኝነት ወጣቶችን በማህበረሰባቸው ውስጥ መልካም ነገሮችን እንዲያበረክቱ ከማስቻሉም በላይ ጠቃሚ የህይወት ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ፣ ርህራሄ እንዲያሳድጉ እና ማህበራዊ ሃላፊነት እንዲሰማቸው እና ለግል እና ለጋራ ህይወታቸው ጠንካራ መሰረት እንዲገነቡ ይረዳል። በበጎ ፈቃድ ስራዎች ውስጥ ሙያዊ እድገት. በበጎ ፈቃድ ተሞክሮዎች፣በትብብር መስራትን፣ ከተለያዩ አካባቢዎች ጋር መላመድ እና በዙሪያቸው ስላለው አለም ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ማግኘትን ይማራሉ።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የዕድገት ደረጃና የአካባቢ ሁኔታ የሚለያይ ነው፡፡የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዜጎች ውስጣቸውከሚሰማቸው ሠብዓዊ አመለካከት ተነስተው ለሚኖሩበት ማህበረሰብ ልማትና ለአካባቢ ደህንነትጊዜያቸውን፣ገንዘባቸውን፣ ጉልታቸውን፣እውቀታቸውንና አመለካከታቸውን የሚያውሉበት በምላሹም ትምህርትና ልምድ የሚያገኙበትና ዕውቀት የሚቀስሙበት ተግባር እንዲሁም ማህበራዊ ግንኙነትንና ትስስርን ያጎለብቱበታል ፡፡
በክልላችንም የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን በክረምትና በበጋ ወቅት በመለየት ወጣቶችን ቀጥተኛ ተዋናይ በማድረግም በርካታ አዎንታዊ ለውጦች እየተመዘገቡ ይገኛሉ ፡፡ በጎነትን ባህል በማድረግ አሁን አሁን ቁጥራቸው በርከት ያሉ ወጣቶች በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ስራዎች በመሳተፍ የዜጎችን ህይወት የመታደግ መልካም ስራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ ፡፡
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የበጎ ፈቃድ ስራዎች ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ በተለያዩ ዘርፎች ሲሰራበት ቆይቷል ፡፡ ይህንን የወጣቶች በጎ ፈቃድ ስራዎች በማጠናከር በ2015 ዓ/ም እንዲሁ ተጠናክሮ መቀጠሉን በሴቶች፣ወጣቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ራሄል ለዊ ተናግረዋል ፡፡ በ2015 ዓ/ም በነበረው የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን በማስፋትና ዕጥረቶችን በመለየትም በ2016 ዓ/ም በክረምና በበጋ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት በ13 የስምሪት መስኮች ዕቅድ በማውጣት ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል ፡፡
በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በ13 ስምሪት መስኮች 601,303 ወጣቶችን በማሳተፍ 1,162,800 የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ በማድረግ 430,236,000 ብር ከመንግሥት ካዝና ይወጣ የነበረዉን ለማትረፍ ታቅዶ ወ 341,184 ሴ 258,409 ድ 599,593 99% ወጣቶችን በማሳተፍ ከ1,956,267 (100%) በላይ የህ/ሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ በማድረግ 511,958,862 ብር ከወጭ ማትረፍ እንደተቻለም ወ/ሮ ራሄል ለዊ ተናግረዋል ፡፡
ለአብነትም የአረጋዊንን ቤትማደስ፣የደም ልገሳ፣የአካባቢጥበቃ ስራዎች፣የተለያዩ የአገልግሎት ስራዎች እና ሌሎች ተግባራት ተጠቃሽ ናቸው ፡፡
በ2016 በጀት ዓመት የበጋ ወራት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተመሳሳይ በ13 የስምሪት መርሐ-ግብር 91,270 በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በማሰማራት 188,500 የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ በማድረግ 47,950,108 ብር የሚገመት አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ እስካሁን በ11 የትግበራ መስኮች አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል፡፡
በዚህም በክረምቱ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞች ቤት ዕድሳትና ግንባታ አፈፃፀም በተመለከተ አዲስ 250 ጥገና 285 በድምር 535 ቤቶችን ለመስራት ታቅዶ አዲስ ቤት 453 ጥገና 400 በድምር 853 ቤቶች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡
በዚህ የተሳታፉ ወ 33,110 ሴ 17,908 ድ 51,018 ሲሆኑ 2,568 የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለና በገንዘብ ሲተመንም 31,551,000 ብር ከወጪ ማዳን መቻሉን ተናግረዋል ፡፡
ወጣቶች ሌላው በተለያዩ አደረጃጀቶች ተሰማሩበት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማዕድ ማጋራትና ያለንን ከማካፈል አንፃር 12,994 የህብረተሰብ ክፍሎችን 3,475,903 ብር ወጪ በማድረግ ማዕድ ማጋራት እንደቻሉም አብራርተዋል ፡፡
በተጨማሪም የአልባሳት የምግብ እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍ በየአደረጃጀቱ የሚደረግ ሲሆን በተለይ የእምነት በዓላትን መሰረት በማድረግ የሚደረጉ ድጋፎች በክልላችን ባህል እየሆነ መምጣቱ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር ነዉ ሲሉም ወ/ሮ ራሄል ለዊ ተናግረዋል፡፡
ሌላዉ በክልላችን በሚገኙ ሁሉም ዞኖች የበጎ ፈቃድ ማህበራት እየተፈጠሩ በመሆናቸዉ እንደ ምርጥ ተሞክሮ ወስደን በሁሉም የክልላችን አከባቢዎች ለማስፋት እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *