ቶኪ በአን በመጠበቅ እና በማልማት ለመጭው ትውልድ ማስተላለፍ ይገባል። ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
የዳውሮ ብሄር የዘመን መለወጫ (ቶኪ በአ) በመጠበቅና በማልማት ለመጭው ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገልጸዋል።




ርዕሰ መስተዳድሩ አክለው፥ የቶኪ በአ ማህበራዊ ዕሴት የኾኑ ሠላም፣ አንድነት፣ ፍቅርና መተሳሰብ በማጠናከር ለሁለንተናዊ ለውጥ መትጋት እንደሚገባ ተናግረዋል።
የዘንድሮው ቶኪ በዓ በዓል የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የመቻል ተምሳሌት የኾነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ ለምረቃ ዝግጁ በኾነበት ማግስት መኾኑ ልዮ እንደሚያደርግ ዶ/ር ነጋሽ ጠቁመዋል።
ቶኪ በአ በብሄረሰብ ዘንድ በየአመቱ ያለፈውን ዓመት በመዘከር እና አዲሱ አመት የሠላምና የጥጋብ እንዲሆን በፍቅር እና በደስታ የሚቀበሉት ክብረ በዓል እንደሆነ ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።
ቶኪ በአ የተነፋፈቁ የሚገናኙበት፣ ወዳጅ ከዘመድ የሚጠያየቁበት ህጻናትና ወጣቶች ህብረ ዝማሬ የሚደምቁበት፤ አባቶች በምረቃት የሚቀበሉበት በዓል እንደሆነም ነው ዶ/ር ነጋሽ የገለጹት።
የቶኪ በአን ዕሴት በማጉላት ለሀገራዊ ክልላዊ አንድነት እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ በማሳደግ የብልጽግና ጉዞ ማሳለጥ እንደሚገባም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ ያስገነዘቡት።
ቶኪ በአ የሙላት እና የጥጋብ፣ የአንድነትና የሠላም እንዲሁም የአዲስ አመት ብስራት ምኞት መግለጫ መኾኑ የገለጹት የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ በዓሉን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ በማይዳሰስ ቅርስነት ለማስገንዘብ እንቅስቃሴ መጀመሩን ተናግረዋል።
በዓሉን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ ለማስመዝገብ በሚደረገው ጥረት አስተዋጽኦ እያደረጉ ለሚገኙ ተቋማት ዋና አስተዳዳሪው አመሥግነዋል።
የቶኪ በአ በዓል ከጥንት ከአባቶች ስወራረስ የመጣ የብሄረሰቡ ደማቅ በዓል መኾኑን ያነሱት የዞኑ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መመሪያ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ደምሰ የቶኪ በአ ማህበራዊ ዕሴቱ ለማጠናከር በዘርፉ አበርክተው እያደረጉ ያሉ አካላትን አመሠግናለሁ።
በበዓሉ የተገኙት የአጎራባች ክልል የጅማ፣ የጋሞ እና ወላይታ ዞኖች የፍቅር መገለጫ ስጦታ ሰጥተዋል።
በዕድገቱ በዛብህ
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
